የወጣቶች ሰብአዊ መብቶች ሲባል፣ ወጣቶች መሰረታዊ መብቶችና ነፃነቶችን ምንም አይነት ልዩነት ሳይደረግባቸው ሙሉ በሙሉ መጠቀማቸውን የሚገልጽ ነው፡፡ (ወጣቶችና ሰብአዊ መብቶች፣ እ.ኤ.አ. በ2018 የተ.መ.ድ. ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽነር ጽ/ቤት ያወጣው ሪፖርት)
የአፍሪካ ወጣቶች ቻርተር አንቀጽ 2፤
ማንኛውም ወጣት የሆነ ሰው ከየትኛውም ዘር፣ ብሔር፣ ቀለም፣ ጾታ፣ ቋንቋ፣ ሃይማኖት፣ ፖለቲካ ወይም ሌላ አስተሳሰብ፣ ብሔራዊ ወይም ማኅበራዊ መሰረት፣ ዕድል፣ ትውልድ ወይም ሌላ ደረጃ መገኘቱ ግንዛቤ ውስጥ ሳይገባ በዚህ ቻርተር የተደነገጉትንና የተጠበቁትን መብቶችና ነፃነቶች የመጠቀም መብቱ ሊረጋገጥለት ይገባል፡፡
ኢትዮጵያ የአፍሪካ ወጣቶች ቻርተርን በአዋጅ ቁጥር 817/2006 አጽድቃለች፡፡
Photo credit: UNICEF Ethiopia