የተ.መ.ድ. የኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊ እና የባህል መብቶች ኮሚቴ፣ አጠቃላይ ትንታኔ ቁጥር 15
ሁሉም ሰው ለግሉ እና ለቤት ውስጥ አገልግሎት በቂ የሆነ፣ ደኅንነቱ የተጠበቀ፣ ተቀባይነት ያለው፣ በአካል ተደራሽ እና በዋጋ ተመጣጣኝ የሆነ ውሃ የማግኘት መብት አለው።
የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 90
የሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የንጹሕ ውሃ፣ የመኖሪያ፣ የምግብና የማኅበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ይደረጋል።