የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 29
ማንኛውም ሰው ያለ ማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት አለው።
የፕሬስ እና የሌሎች የመገናኛ ብዙኃን፣ እንዲሁም የሥነ ጥበብ ፈጠራ ነጻነት ተረጋግጧል። የፕሬስ ነጻነት በተለይም የቅድመ ምርመራ በማናቸውም መልኩ የተከለከለ መሆኑን እና የሕዝብን ጥቅም የሚመለከት መረጃ የማግኘት መብቶችን ያጠቃልላል።
የመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ቁ. 1238/2013፣ አንቀጽ 86(1)
በመገናኛ ብዙኃን አማካኝነት የወንጀል ድርጊት በመፈጸም የተጠረጠረ ማንኛውም ሰው ወይም አካል በወንጀል ሥነ ሥርዓት ሕግ ድንጋጌዎች መሠረት ለተጨማሪ ምርመራ በእስር እንዲቆይ ሳይደረግ ክሱ በቀጥታ በዐቃቤ ሕግ አማካኝነት ለፍርድ ቤት መቅረብ አለበት፡፡