Skip to content
Facebook Twitter
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social and Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants Rights
        • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
        • Women’s and Children’s Rights
        • HR Monitoring and Investigation
        • Human Rights Education
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል፣ በዲራሼ ልዩ ወረዳ የተፈጠረው ግጭት እና ያስከተለው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት አስቸኳይ፣ ሁሉን አቀፍ ዘላቂ መፍትሔ ይፈልጋል

December 2, 2022December 3, 2022 Event Update

በግጭቱ የተጎዳን ማኅበረሰብ የመፍትሔው አካል ማድረግ ለጥረቱ ስኬት ወሳኝ ሚና አለው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦች እና ሕዝቦች ክልል የቀድሞ የሰገን አካባቢ ሕዝቦች ዞን በ2011 ዓ.ም. መፍረሱን ተከትሎ በዲራሼ ልዩ ወረዳ ከመዋቅር እና የማንነት ጥያቄ ጋር በተያያዘ፣ በተፈጠሩ ግጭቶች የሰዎች ሞት፣ መፈናቀል እና ከፍተኛ የንብረት ውድመት ደርሷል፡፡ 

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአካባቢው በተፈጠረው ግጭት ላይ ክትትል እና ምርመራ በማድረግ ከክልሉ መንግሥት ጋር በቅርበት ሲሠራ ቆይቷል። ግጭቱ የተወሳሰበ እና ዘርፈ ብዙ እንደመሆኑ መጠን አካታች (inclusive)፣ ሁሉን አቀፍ (comprehensive) እና ዘላቂ መፍትሔ ሊፈለግለት የሚገባ በመሆኑ ይህ እንዲደረግ ኢሰመኮ ጥረት ሲያደርግ ቆይቷል፡፡

ግጭቱን በዘላቂነት ለማስቆም እና በግጭቱ ምክንያት የሚፈጠሩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለማስቀረት ኢሰመኮ ግጭቱ ከተከሰተ ጊዜ ጀምሮ ያደረጋቸው የክትትል እና የምርመራ ግኝቶችን መሰረት በማድረግ የተለዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ቀርበው ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ ማምጣት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የማኅበረሰብ ተወካዮች እና ተገቢነት ያላቸው የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በተገኙበት ሐምሌ 22 ቀን 2014 ዓ.ም. በሃዋሳ ከተማ የምክክር መድረክ ማዘጋጀቱ ይታወሳል።

የዚሁ የምክከር መድረክ ቀጣይ የሆነው ሁለተኛ ዙር የምክክር መድረክ ኅዳር 17 እና 18 ቀን 2015 ዓ.ም. ከሁሉም የልዩ ወረዳው ብሔረሰቦች የተወጣጡ ተወካዮች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የወጣቶች፣ የሴቶች እና የሲቪል ማኅበራት ተወካዮች፣ የወረዳው አስተዳደር፣ የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ፣ የክልሉ የልዩ ኃይል ፖሊስ፣ የክልሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ፣ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ ፍትሕ እና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የፍትሕ ሚኒስቴር እና የሰላም ሚኒስቴር በተገኙበት በአርባ ምንጭ ከተማ የሁለት ቀናት ውይይት ተደርጓል፡፡

በመጀመሪያው ቀን ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉም አካላት በተገኙበት የኢሰመኮ የክትትል እና ምርመራ ግኝቶች ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል። በሁለተኛው ቀን  የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ተወካዮች ብቻ የተሳተፉበት በመጀመሪያው ቀን የቀረቡ የምርመራ እና ክትትል ግኝቶችን እንዲሁም ከተሳታፊዎች የተሰጡ አስተያየቶችን መሰረት በማድረግ በቀጣይ በአካባቢው የተፈጠረውን ግጭት በዘላቂነት ለማስቆም እና የነዋሪዎችን ሰብአዊ መብቶች ለማስከበር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በመምከር የድርጊት መርኃ ግብር የማዘጋጀት ሥራ ተሰርቷል፡፡ የድርጊት መርኃ ግብሩ ሰላም ለማስፈን፣ ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ፣ እርቅ ለማውረድ፣ መልሶ ማቋቋም እና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦትን የተመለከቱ በቀጣይ መሠራት ያለባቸው አራት ዋና ዋና ተግባራትን የያዘ ነው፡፡  

የተዘጋጀው የድርጊት መርኃ ግብር ዝርዝር የአፈጻጸም እቅድ ተዘጋጅቶለት በክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ መሪነት እና ተገቢነት ባላቸው ሌሎች ቢሮዎች ፈጻሚነት ተግባራዊ እንዲደረግ መግባባት ላይ ተደርሷል። በተጨማሪም ከማኅበረሰብ ተወካዮች በቀረበው ጥያቄ መሰረት በዚህ መድረክ የተዘጋጀውን የድርጊት መርኃ ግብር አፈጻጸም የሚከታተል እና እንደ አስፈላጊነቱ የቴክኒክ ድጋፍ የሚያደርግ ሱፐርቫይዘሪ ኮሚቴ ተቋቁሟል፡፡

የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ምርመራ እና ክትትል ሪጅናል ዳይሬክተር ኢማድ አብዱልፈታህ፣ የክልሉ መንግሥት እና ማኅበረሰቡ ችግሩን ለመፍታት ያሳዩት ተነሳሽነት የሚደነቅ መሆኑን ገልጸው፤ ለእቅዱ መሳካት ሰላም የማስፈን፣ ተጠያቂነትን የማረጋገጥ፣ እርቅ የማውረድ፣ መልሶ ማቋቋም እና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ሥራዎች በቀረበው የድርጊት መርኃ ግብር መሰረት በአንድ ማዕቀፍ ስር ተግባራዊ እንዲደረጉ አጽንኦት ሰጥተው ጠይቀዋል፡፡

ኢሰመኮ ይህ እቅድ እንዲሳካ እና በአካባቢው የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት በዘላቂነት እንዲቆሙ ጉዳዩ የሚመለከታቸው የክልል እና የፌዴራል የመንግሥት አካላት ግጭቱ ያስከተለውን የማኅበራዊ እና ሰብአዊ ቀውስ በመረዳት ለጥረቱ መሳካት ድርሻቸውን በኃላፊነት እንዲወጡ እያሳሰበ፤ የተዘጋጀውን የድርጊት መርኃ ግብር አፈጻጸም በቅርበት መከታተሉንና እና መደገፉን የሚቀጥል መሆኑን ይገልጻል፡፡

Location SNNP

Reports & Press Releases

October 6, 2022October 7, 2022 Event Update
የሲቪል ማኅበራት ከአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ኮሚሽን ጋር የሚኖራቸው የሥራ ግንኙነት እንዲጠናከር እንዲሁም ለኮሚሽኑ በሚቀርበው ወቅታዊ የመንግሥት ዘገባና የግምገማ ሂደት ውስጥ ያላቸው ሚና ላይ የተዘጋጀ አውደ ጥናት
August 25, 2021February 20, 2022 EHRC Quote
ኢሰመኮ በአማራ ክልል የባለሞያ ቡድን ሊያሰማራ ነው
March 23, 2022March 24, 2022 የሰብአዊ መብቶች ጽንሰ-ሀሳብ
የሴቶችን ሁለንተናዊ ተሳትፎ ማረጋገጥ
December 25, 2020May 22, 2021 Press Release
Konso Zone: Recurring conflict and Human rights crisis

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
EHRC
We are an independent national human rights
institution tasked with the promotion & protection of
human rights in Ethiopia
Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org

© 2023 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in settings.

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Gambella
    • Oromia
    • Somali
    • SNNP
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social and Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants Rights
    • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
    • Women’s and Children’s Rights
    • HR Monitoring and Investigation
    • Human Rights Education
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
Facebook Twitter
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.