Skip to content
Facebook Twitter
  • አማርኛአማርኛ
  • EnglishEnglish
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • SNNP
        • Tigray
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social and Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants Rights
        • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
        • Women’s and Children’s Rights
        • HR Monitoring and Investigation
        • Human Rights Education
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Videos
    • Newsletters
    • Events
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ ለሰብአዊ መብቶች መከበር አስተዋጽኦ ሊያደርጉ ይገባል ሲል ኢሰመኮ ጥሪ አቀረበ

May 11, 2022May 16, 2022 Press Release

ለሰብአዊ መብቶች ጥሰት ተጠያቂነትን በማረጋገጥ፣ የሕግ በላይነትን በማስፈን፣ መንግሥትና የስራ አስፈጻሚ አካላቱ በመሉ ለሰብአዊ መብቶች መከበር፣ መጠበቅና መሟላት ያላቸውን ቁርጠኝነት እንዲያድሱና እንዲተገብሩ ልዩ ትኩረትና ክትትል ይሻል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የ10 ወር የሥራ ክንውን ሪፖርቱን ግንቦት 3 ቀን 2014 ዓ.ም. ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ የፍትሕ እና የዲሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረበበት ወቅት የኮሚሽኑ የአምስት ዓመት የስትራቴጂ እቅድ የመጀመሪያ የትግበራ ዓመት እንደመሆኑ መጠን፣ ዋና ዋና ተግባራት ተብለው ከተለዩ የሰብአዊ መብቶች ሥራዎች ጎን ለጎን በርካታ የተቋም ግንባታ ሥራዎች መከናወናቸውን አስታውሷል። በዚህ ረገድ የኮሚሽኑን አካላዊና ዲጂታል ተደራሽነት የማሻሻል፣ በሰፊ ጥናት ላይ የተመሰረተ አዲስ  መዋቅር በመተግበር ተቋሙን በሰው ኃይል ማብቃት፣ የበጀት ነጻነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችሉ አሰራሮችንና ደንቦችን በመቅረጽና ለሥራው አስፈላጊ የሆነ ሃብት በማሰባሰብ የኮሚሽኑን የፋይናንስ አቅም የማሻሻልና እንዲሁም ከሌሎች አቻ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማትም ሆነ ከአህጉራዊና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የተዘረጉ የትብብር ሥራዎች በዝርዝር ቀርበዋል።  

በተጨማሪም በኢሰመኮ ሪፖርት ከተጠቀሱ በክትትልና ምርመራ ሥራዎቹ ባለፉት 10 ወራት ከተከናወኑ ሥራዎች ውስጥ በተለይ ግጭት የተከሰተባቸው 65 ቦታዎችን መድረሱን፣ ባለፉት 3 ወራት ብቻ 450 ሺህ ስደተኞችን የሚያስጠልሉ አስር ስደተኛ ካምፖች ላይ የክትትል ሥራ ማከናወኑን፣ በአምስት ክልሎች የሚገኙ 1.5 ሚልዮን ገደማ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን የሚያስጠልሉ 47 ጊዜያዊ መጠለያዎች፣ ጣቢያዎችን እና ተቀባይ ማኅበረሰቦችን መጎብኘቱን እና ሪፖርት እና ምክረ ሃሳቦችን እንደየአግባብነቱ በይፋዊ መግለጫ ወይም ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካሎች ማቅረቡ ተገልጿል። 

ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች አያያዝን በተመለከተ፣ በመላ ሀገሪቱ በሚገኙ 82 ማረሚያ ቤቶች እና በ270 ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ማከናወኑንም ከተጠቀሱት የክትትልና የምርመራ ሥራዎች መካከል ናቸው። 

የኢሰመኮ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ኮሚሽኑ የተቋማዊ ግንባታን በተመለከተ ያከናወናቸውን ተግባራት  ገለጻ ሲያደርጉ፣ ኮሚሽኑ በዓለም አቀፍ ደረጃ ብሔራዊ የሰብአዊ መብቶች ተቋማት የሚመሩበትና “የፓሪስ መርሆዎች” ተብለው በሚታወቁት መስፈርቶች/መርሆች መሰረት የሚጠበቅበትን ሙሉ በሙሉ በማሟላቱ የደረጃ አንድ (A Status) እውቅና ያገኘው ባለፉት 10 ወራት መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በበኩላቸው ኮሚሽኑ በሪፖርቱ ወቅት ባከናወናቸው ተግባራት አማካኝነት የለያቸውንና ምክር ቤቱ ልዩ ትኩረት ሊሰጣቸው የሚገባቸውን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎችንና ምክረ ሃሳቦችንም አቅርበዋል። 

በተለይ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በተከሰተው ጦርነት እንዲሁም በሌሎች የሀገራችን ክፍሎች ከብሔር ማንነት፣ ራስን በራስ የማስተዳደርና የአስተዳደር አካባቢዎች ወሰን አልፎ አልፎም ከሃይማኖት ጥያቄ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ወቅቶች በሚያገረሹ ግጭቶች ሳቢያ ጾታዊና ወሲባዊ ጥቃቶችን ጨምሮ እጅግ በርካታ ሰዎች ለሞት፣ ለአካልና ለሥነልቡና ጉዳት፣ ለመፈናቀልና፣ ለንብረት ውድመት መዳረጋቸውን አስምረውበታል። በመሰረተ ልማቶች ላይ በደረሰ ውድመትም መሰረታዊ አገልግሎቶች መቋረጣቸውን፣ ከፍተኛና መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች መፈጸማቸውን፤ ይህን አይነት የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ስጋትም እንደቀጠለ አስታውሰው፤ በትግራይ ክልል ተጀምሮ ወደ አፋርና አማራ ክልል ተስፋፍቶ የነበረው ጦርነት አሁን ላይ መብረዱና የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት መሻሻሉ ተስፋ ሰጪ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፤ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦቱ በፍላጎቱ መጠን የተሟላ እንዲሆን፣ መሰረታዊ አገልግሎቶች ወደ ነበሩበት ቦታ እንዲመለሱ፣ ዘላቂ ሰላማዊ መፍትሄና ፍትሕ እንዲረጋገጥ ገና ብዙ እርምጃዎችና ሥራዎች እንደሚቀሩ ገልጸዋል፡፡  

ባለፉት አስር ወራት በተለያዩ ወቅቶች ከሕግ ውጪ የተፈጸሙ ግድያዎች፣ ከመጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም፣ የዘፈቀደና ከፍርድ ወይም ክስ በፊት ያለ የተራዘመ እስር፣ በጋዜጠኞችና በፖለቲካ ተቃዋሚዎች ላይ ያነጣጠረ እስራት እና የአንዳንድ እስር ቦታዎች አያያዝ ሁኔታ አሳሳቢነት እየጨመረ በመምጣቱ የምክር ቤቱን ልዩ ትኩረት እንደሚሻ ተገልጿል፡፡ 

በጦርነትና በግጭት እንዲሁም በሌሎች ምክንያቶች የተጎዱ የመሰረተ ልማት አውታሮችን መልሶ ከማቋቋም ጎን ለጎን ሀገራዊው ኢኮኖሚያዊ ሁኔታና የኑሮ ውድነት፤ እንዲሁም በልዩ ልዩ ማህበራዊና መንግስታዊ አገልግሎቶች አሰጣጥ የሚሰማው የሕዝብ ቅሬታ ለሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ አደጋና ስጋት በመሆኑ የቅርብ ክትትል የሚሹ ጉዳዮች መሆናቸውም ሪፖርት ተደርጓል። 

ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በማጠቃለያቸው ሁሉም የምክር ቤቱ አባላት፤ በየደረጃው ያሉ የመንግሥት አስፈጻሚ አካላትና ኃላፊዎች ላይ እንዲሁም የፖለቲካ ፓርቲዎችና ኃላፊዎች ላይ የቅርብ ክትትል በማድረግ፣ በመጠየቅና በማስፈጸም፣ ለሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ በመስጠት የበኩላቸውን አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

Reports & Press Releases

December 10, 2021December 10, 2021 EHRC Quote
Join us and Stand Up for Human Rights on Human Rights Day
November 20, 2021February 20, 2022 ኢሰመኮ በመገናኛ ብዙኃን
ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ሽልማታቸዉን ተቀበሉ – Deutsche Welle
June 18, 2021July 13, 2021 ጋዜጣዊ መግለጫ
በምርጫው ወቅት የሕግ አስከባሪ አካላት ሰብአዊ መብቶችን አክብረው መንቀሳቀስ አለበቸው
November 24, 2020May 30, 2021 ሪፖርት
በትግራይ ክልል፣ አክሱም ከተማ የተፈጸመው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ምርመራ የመጀመሪያ ደረጃ (ቀዳሚ) ሪፖርት

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup

Signup for the Latest Update from EHRC

    Submit your email here to get the latest update from EHRC.

    Facebook Like us on FacebookTwitter Follow us on Twitter

    Useful Links

    • NANHRI
    • GANHRI
    • OHCHR
    • ACHPR

    Get Involved

    • Jobs
    • Events
    • Contact Us
    • Telegram Bot

    Connect with Us

    • Facebook
    • Twitter
    • LinkedIn
    • YouTube
    EHRC
    We are an independent national human rights
    institution tasked with the promotion & protection of
    human rights in Ethiopia
    Submit your email to get the latest update from EHRC

    © 2022 Copyright Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). All Rights Reserved. Powered by 360Ground

    This website uses cookies in order to improve the user experience and provide additional functionality.

    By continuing to use this site you agree to our use of cookies.

    Scroll to top
    • About
      • Who We Are
      • Our Team
      • Careers
      • Contact Us
    • Regions
      • Addis Ababa
      • Afar
      • Amhara
      • Benishangul Gumuz
      • Gambella
      • Oromia
      • Somali
      • SNNP
      • Tigray
    • Areas of Work
      • Economic, Social and Cultural Rights
      • Civil & Political Rights
      • IDPs, Refugees & Migrants Rights
      • Rights of Persons with Disabilities and the Rights of Older Persons
      • Women’s and Children’s Rights
      • HR Monitoring and Investigation
      • Human Rights Education
    • Press Releases
    • Reports
    • Media
      • EHRC on the News
      • EHRC Videos
      • Newsletters
      • Events
    • Resources
    • አማርኛአማርኛ
    • EnglishEnglish
    Facebook Twitter
    Search
    Powered by  GDPR Cookie Compliance
    Privacy Overview

    This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

    Strictly Necessary Cookies

    Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

    If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.