ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ መግቢያና አንቀጽ 1
- የሁሉንም የሰው ዘር አባላት በተፈጥሮ የተገኘ ክብር እንዲሁም እኩል እና የማይገፈፉ መብቶች ዕውቅና መስጠት በዓለም ላይ ለነጻነት፣ ፍትሕ እና ሰላም መሠረት ነው።
- ሰዎች ሁሉ እኩል ክብርና መብቶች ይዘው ነጻ ሆነው ተፈጥረዋል። የማመዛዘን ችሎታን እና ኅሊናን በተፈጥሮ ስለታደሉ እርስ በርሳቸው በወንድማማችነት መንፈስ ሊተያዩ ይገባል።
የሁሉንም የሰው ዘር አባላት በተፈጥሮ የተገኘ ክብር እንዲሁም እኩል እና የማይገፈፉ መብቶች ዕውቅና መስጠት በዓለም ላይ ለነጻነት፣ ፍትሕ እና ሰላም መሠረት ነው
ሁሉ አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ፣ መግቢያና አንቀጽ 1