የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ በአንቀጽ 5
- አባል ሀገራት የሴቶች ሰብአዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ከተሰጣችው መስፈርቶች ጋር የሚጣረሱ ሁሉንም ዐይነት ልማዳዊ ድርጊቶች መከልከልና ማውገዝ አለባቸው።
- አባል ሀገራት ቅጣትን የሚያስከትሉ ሕጎችን በማውጣት ማንኛውንም ዐይነት የሴት ልጅ ግርዛትን መከልከል አለባቸው።
- የሴት ልጅ ግርዛት እና ተያያዥ ድርጊቶች በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የወንጀል ሕግ፣ አንቀጽ 565 እና አንቀጽ 566 ላይ የሚያስቀጡ ተግባራት ናቸው።