በአፍሪካ የሰዎችና የሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል፣ በአንቀጽ 5 

  • አባል ሀገራት የሴቶች ሰብአዊ መብቶች ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ የሚያሳድሩ እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ከተሰጣችው ድንጋጌዎችንና መስፈርቶችን የሚጣረሱ ማናቸውንም ዓይነት ልማዳዊ ድርጊቶች መከልከልና ማውገዝ አለባቸው። 
  • አባል ሀገራት ቅጣትን የሚያስከትሉ ሕጎችን በማውጣት ማንኛውንም ዓይነት የሴት ልጅ ግርዛትን መከልከል አለባቸው።

የሴት ልጅ ግርዛት እና ተያያዥ ድርጊቶች በኢ.ፌ.ዴ.ሪ የወንጀል ሕግ፣ አንቀጽ 565 እና  አንቀጽ 566 መሠረት የሚያስቀጡ ተግባራት ናቸው።