በአፍሪካ ሕዝቦችና ሰዎች መብቶች ቻርተር የአፍሪካ አረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 14

አባል ሀገራት፦

  • በተፈጥሮ አደጋዎች፣ በግጭት ወቅት፣ በጦርነት ወይም በእርስ በእርስ ግጭቶች ጊዜ ተጎጂዎችን ከአደጋ ለመጠበቅ  በሚደረግ ጥረት፣ መልሶ በማቋቋም፣ በሰፈራ እና በሚወሰዱ ሌሎች እርምጃዎች ወቅት ለአረጋውያን ቅድሚያ የመስጠት ግዴታ አለባቸው።
  • አረጋውያን በሁሉም ጊዜ ሰብአዊ እንክብካቤ፣ ጥበቃ እና ክብር እንዲያገኙ የማድረግ እና የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዳይነፈጋቸው የማድረግ ግዴታ አለባቸው።

የካምፖላ ኮንቬንሽን፣ አንቀጽ 9(2፣ሐ)

  • አባል ሀገራት በሀገራቸው ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች በተለይም ልዩ ድጋፍ ለሚያሻቸው አረጋዉያንና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ልዩ ጥበቃና ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል።