በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት፣ አንቀጽ 7 (ሀ) – (ሐ)
ይህን ስምምነት የተቀበሉ ሀገራት ሴቶች በሀገሪቱ የፖለቲካ እና ሕዝብ ነክ ሕይወት ውስጥ የተሟላ ተሳትፎ እንዳይኖራቸው የሚያሰናክል ልዩነትን ለማጥፋት ተገቢ እርምጃዎችን ሁሉ ይወስዳሉ። በተለይም የሴቶችን ከወንዶች እኩል፦
- በሁሉም ምርጫዎችና ሕዝበ ውሳኔዎች ድምጽ የመስጠት እና ለማናቸውም በሕዝብ ለሚመረጡ መንግሥታዊ አካላት ዕጩ ተመራጭ የመሆን፤
- የመንግሥት ፖሊሲን በመቅረጽና በማስፈጸም ሂደት ውስጥ የመሳተፍ፣ የመንግሥት ሥልጣን የመያዝ፣ በማናቸውም የመንግሥት እርከን ውስጥ ኃላፊነትን ተረክቦ የመሥራት፤
- በማናቸውም የሀገሪቱ የፖለቲካና የሕዝብ ሕይወት በሚመለከታቸው መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች እና ማኅበራት ውስጥ የመሳተፍ መብቶች ያረጋግጣሉ።