የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 4(1) እና (2(ሀ እና ለ)) 

  • ማንኛዋም ሴት ለሕይወቷ እና ለአካል ደኅንነቷ ክብር የማግኘት መብት አላት፡፡ ሁሉም ዐይነት ብዝበዛ፣ ጨካኝ፣ ኢ-ሰብአዊ ወይም ክብርን የሚያዋርድ ቅጣት እና አያያዝ የተከለከለ ነው። 

አባል ሀገራት ውጤታማና ተገቢ እርምጃዎችን ለመውሰድ:-

  • ያልተፈለገ ወይም የግዳጅ ወሲብን ጨምሮ በተገለለም ቦታ ሆነ በግልጽ በሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ሁሉንም ዐይነት ጥቃቶች ለመከላከል ሕጎችን ማውጣትና ማስፈጸም አለባቸው፤
  • በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ማንኛውንም ዐይነት ጥቃት ለመከላከል፣ ለመቅጣትና ለማስወገድ እንደ አስፈላጊነቱ ሌሎች ሕጎችን ማውጣት፣ አስተዳደራዊ፣ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ እርምጃዎችን መውሰድ ይኖርባቸዋል።