የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 10 (1) እና (2) (ሀ) (ለ) (ሠ)
- ሴቶች በሰላም የመኖር እንዲሁም ሰላምን በማስፋፋትና በማስጠበቅ ሥራዎች ላይ የመሳተፍ መብት አላቸው።
- አባል ሀገራት፦
- ለሰላም እና ለሰላም ባህል በሚሰጡ የትምህርት መርኃ ግብሮች፣
- በአካባቢ፣ በሀገር፣ በቀጠና፣ በአህጉር እና በዓለም አቀፍ ደረጃ ባሉ የግጭት መከላከል፣ አስተዳደር እና አፈታት መዋቅሮች እንዲሁም የአሠራር ሂደቶች፣
- በሁሉም የድኅረ ግጭት የመልሶ ግንባታ እና የመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ዕቅድ፣ ዝግጅት እና ትግበራ ዘርፎች የሴቶችን ከፍ ያለ ተሳትፎ ለማረጋገጥ ተገቢውን እርምጃ ሁሉ መውሰድ አለባቸው።