በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ዓለም አቀፍ ስምምነት፣ አንቀጽ 3
- አባል ሀገራት በሁሉም መስክ በተለይም በፖለቲካዊ፣ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ መስኮች የሴቶችን ሁለንተናዊ እድገት ለማረጋገጥና ከፍ ለማድረግ እንዲሁም ሴቶች ከወንዶች እኩል በሰብአዊ መብቶቻቸው እና መሠረታዊ ነጻነቶቻቸው መጠቀም እንዲችሉ ሕግ ማውጣትን ጨምሮ አግባብነት ያላቸውን እርምጃዎች ሁሉ መውሰድ አለባቸው።
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 35(3)
- ሴቶች በበታችነትና በልዩነት በመታየታቸው የደረሰባቸውን የታሪክ ቅርስ ከግምት ውስጥ በማስገባት ይህ ቅርስ እንዲታረምላቸው፤ በተጨማሪ የድጋፍ እርምጃዎች ተጠቃሚ የመሆን መብት አላቸው። በዚህ በኩል የሚወሰዱት እርምጃዎች ዓላማ በፖለቲካዊ፣ በማኅበራዊና በኢኮኖሚያዊ መስኮች እንዲሁም በመንግሥት እና በግል ተቋሞች ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት ተወዳዳሪና ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማድረግ እንዲቻል ልዩ ትኩረት ለመስጠት ነው።