የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የአካል ጉዳተኞች መብቶች ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 5 (1)
- ማንኛውም አካል ጉዳተኛ ሰው ዘርን፣ ጎሳን፣ የቆዳ ቀለምን፣ ጾታን፣ ቋንቋን፣ ሃይማኖትን፣ ፖለቲካን ወይም በሌላ ዐይነት አመለካከት፣ በብሔራዊ ወይም ማኅበራዊ መሠረትን፣ ሃብትን፣ ትውልድን ወይም ሌላ ሁኔታን ጨምሮ በማንኛውም ምክንያት ማንኛውም ዐይነት ልዩነት ሳይደረግበት በዚህ ፕሮቶኮል ውስጥ ዕውቅናና ዋስትና የተሰጣቸው መብቶች እና ነጻነቶችን የማግኘት እና የመጠቀም መብት አለው።
የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 5 (2)
- ተዋዋይ ሀገራት አካል ጉዳተኝነት ላይ ተመሥርቶ የሚፈጸም ሁሉንም ዐይነት አድሎአዊ ልዩነት መከልከል እና አካል ጉዳተኞች በማንኛውም ሁኔታ ከሚደረግ አድሎአዊ ልዩነት እኩልና አስተማማኝ የሕግ ጥበቃ ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።