የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደኅንነት ቻርተር፣ አንቀጽ 24 (1 እና 6) 

የጉዲፈቻ ሥርዓትን የተቀበሉ አባል ሀገራት የሕፃኑ ጥቅም ከሁሉም በላይ ቅድሚያ  የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው። እንዲሁም:- 

  • የጉዲፈቻን ጉዳይ ለመወሰን ሥልጣን የተሰጣቸው አካላትን ማቋቋም እና ጉዲፈቻው ተፈጻሚነት ካላቸው ሕጎች እና ሥነ-ሥርዓቶች  ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲሁም አግባብነት ባላቸው አስተማማኝ  መረጃዎች  መሠረት  መከናወኑን እና  የሕፃኑ ወላጆች፣ዘመዶች ወይም አሳዳጊዎች አስፈላጊ ሲሆን አግባብነት ያላቸው የሚመለከታቸው ሰዎች ተገቢ ምክር ላይ በመመሥረት ጉዲፈቻውን መቀበላቸውን ማረጋገጥ እና 
  • የጉዲፈቻ ልጁን ደኅንነት ለመከታተል የሚያስችል አሠራር መዘርጋት አለባቸው።