Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

ለ4ኛው የኢሰመኮ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የጥበብ ሥራዎች ውድድር ተጀመረ 

October 14, 2024October 15, 2024 4th Film Festival, Press Release

4ኛው የኢሰመኮ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በሴቶች ሕይወት እና በቂ ምግብና ውሃ በማግኘት መብቶች ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ ሁሉም ሰው በውድድሩ እንዲሳተፍ እና ሂደቱን እንዲከታተል ተጋብዟል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት በየዓመቱ የሚካሄደው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ ጀምሮ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች ይካሄዳል። በፌስቲቫሉ ለሕዝብ ዕይታ የሚቀርቡ የሥዕልና የፎቶግራፍ እንዲሁም የአጫጭር ሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ውድድር ተዘጋጅቷል። ውድድሩ በ2016 ዓ.ም. በኢሰመኮ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት አሳሳቢ ተብለው ከተለዩ መብቶች መካከል በሕይወት የመኖር መብት አሁንም ከፍተኛ ትኩረት የሚሻ ሆኖ በመቀጠሉ፣ በዘንድሮ ዙር በተለይም በሴቶች ሕይወት ላይ በማተኮር፣ በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ዘርፍ ደግሞ በበቂ ምግብና ውሃ በማግኘት መብት ላይ በማተኮር ጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ.ም. በይፋ ተጀምሯል። ውድድሩ በአዲስ አበባ፣ በአዳማ፣ በአርባምንጭ፣ በአሶሳ፣ በባሕር ዳር፣ በሃዋሳ፣ በጋምቤላ፣ በጅግጅጋ፣ በጅማ፣ በመቀሌ እና በሰመራ ከተሞች እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2017 ዓ.ም. ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ ይቆያል።

ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ በኢሰመኮ አዘጋጅነት የሚካሄደው ይህ ዓመታዊ ፌስቲቫል ዓላማ ስለ ሰብአዊ መብቶች በኪነ ጥበብም ሆነ በሌሎች ሥራዎቻቸው የሚያወሱ እና የሚያበረታቱ ሰዎችን፣ ተቋማትን እና ድምፆችን ማሰባሰብ ነው። በተጨማሪም ፌስቲቫሉ ሰዎችን በአንድ ወቅታዊና አንገብጋቢ ጉዳይ ዙሪያ በማስተባበር በሰብአዊ መብቶች ላይ ግንዛቤ ማሳደግ እና በኪነ ጥበብ አማካኝነት ለተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮችን ተደራሽ ለማድረግ ያለመ ነው።

በ2016 ዓ.ም. ለሦስተኛ ጊዜ በተካሄደው ፌስቲቫል ለመጀመሪያ ጊዜ ከፊልም ሥራዎች በተጨማሪ በልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ዘርፎች ለተሰማሩ ጀማሪ እና ልምድ ላላቸው ሰዎች ዕድል ለመስጠት፣ ለማበረታታት እና ለሰብአዊ መብቶች ሥራዎች ድምፅ ለመሆን በማለም የአጫጭር ፊልም እና የፎቶግራፍ ውድድርን አካቶ ከ160 በላይ ሰዎች የኪነ ጥበብ ሥራቸውን ለኢሰመኮ በመላክ ተወዳድረዋል።

ኢሰመኮ በዘንድሮው 4ኛ ዙር ፌስቲቫል ውድድር የሚካሄድባቸውን የኪነ ጥበብ ዘርፎች በማስፋት፣ የኪነ ጥበብ ሥራዎችን ይዘት ጥራት ለማሳደግ የሚረዱ ውድድሮችና መሰል አሳታፊ ዝግጅቶችን በማካተት፣ የሚሳተፉ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎችን እንዲሁም ዝግጅቶቹ የሚካሄዱባቸውን ከተሞች ብዛት በመጨመር የፎቶግራፍ፣ የአጫጭር ሥነ ጽሑፍ ሥራዎች እና የሥዕል ውድድሮችን ያካሂዳል።

የሥዕልና የፎቶግራፍ ውድድሩ ትኩረቱን በቂ ምግብና ውሃ በማግኘት መብቶች ላይ ሲያደርግ የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ውድድር ደግሞ በሕይወት የመኖር መብት በተለይም በሴቶች ሕይወት ላይ የሚያተኩር ነው፡፡ በአጫጭር የሥነ ጽሑፍ ሥራዎች ዘርፍ ለውድድር የሚቀርብ ሥራ ከ 3 ገጽ ያልበለጠ (ከ600 ቃላት ያላነሰ፣ ከ1200 ቃላት ያልበለጠ) ሊሆን ይገባል። በሁለቱም ዘርፎች የሚቀርቡ የጥበብ ሥራዎች ዘጋቢ፣ ምናባዊ ወይም እውነተኛ ታሪክ ላይ መሠረት ያደረጉ ሊሆኑ ይችላሉ።

ፌስቲቫሉ ተሳታፊዎች ለውድድር የተመረጡት የሰብአዊ መብቶች ጉዳዮች መከበር ወይም መጣስ በሰዎች ሕይወት ላይ ያለውን አንድምታ የሚገልጹ፣ የተለያዩ ሐሳቦችን የሚሰጡ፣ ጥያቄዎችን የሚያጭሩ እና ለማሰላሰል የሚጋብዙ የኪነ ጥበብ ሥራዎችን የሚያቀርቡበት ይሆናል። ለውድድር የሚቀርቡ የኪነ ጥበብ ሥራዎች ልዩ ትኩረት የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ማለትም ሕፃናትን እና ታዳጊዎችን፣ ሴቶችን፣ አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን ወይም ስደተኞችን ማእከል እንዲያደርጉ ይጠበቃል።

ውድድሩ የሚካሄድባቸው ከተማዎችና የውድድር ዘርፎች ከዚህ በታች ተገልጸዋል።

ተ.ቁ ከተማ የውድድር ዘርፍ ውድድሩ የሚያተኩርበት ጭብጥ 
 1.አዲስ አበባ የፎቶግራፍ እና የሥነ ጽሑፍ ውድድር የሴቶች ሕይወት እና በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብቶች 
 2.አዳማ የፎቶግራፍ ውድድር በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብቶች 
 3.አርባምንጭ የፎቶግራፍ ውድድር በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብቶች 
 4.አሶሳ የሥዕል ውድድር የሴቶች ሕይወት 
 5.ባሕር ዳር የሥዕል ውድድር የሴቶች ሕይወት 
 6.ሃዋሳ የፎቶግራፍ ውድድር በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብቶች 
 7.ጋምቤላ የሥዕል ውድድር የሴቶች ሕይወት 
 8.ጅግጅጋ የፎቶግራፍ ውድድር በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብቶች 
 9.ጅማ የፎቶግራፍ ውድድር በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብቶች 
 10.መቀሌ የሥዕል ውድድር የሴቶች ሕይወት 
 11.ሰመራ የሥዕል ውድድር በቂ ምግብና ውሃ የማግኘት መብቶች 

ውድድሮቹ በሚካሄድባቸው ከተሞች የሚገኙ ፍላጎት ያላቸው ጀማሪም ሆኑ ልምድ ያላቸው ሰዎች በሙሉ በውድድሮቹ እንዲሳተፉ ተጋብዘዋል። በተጨማሪም መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የመገናኛ ብዙኃን ወይም የስልጠናና ትምህርት ሰጪ ተቋማት በውድድሩ መሳተፍ ይችላሉ።

በሁሉም የኪነ ጥበብ ዘርፎች በውድድሩ ለሚሳተፉ ግለሰቦች እና ተቋማት በሙሉ የዕውቅና ሰርተፊኬት የሚሰጥ ሲሆን፣ በተጨማሪም አሸናፊ ለሚሆኑ ተወዳዳሪዎች ሽልማት ተዘጋጅቷል።

የኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ የኢሰመኮ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ታኅሣሥ 1 ቀን የሚከበረውን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች ቀን ታሳቢ በማድረግ የሚዘጋጅ መሆኑን ጠቁመው፣ “ዘንድሮ ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄደው ይህ ፌስቲቫል በጥበብ ሥራዎች ለሰብአዊ መብቶች ጉዳይ ድምፅ ለመሆን እና ‘ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን’ ማየት የሚለውን የኢሰመኮን ራዕይ ለማሳካት በጋራ የምንሰባሰብበት ነው” ብለዋል። አክለውም በውድድሩ በተለይም ወጣቶች እና ታዳጊዎች እንዲሁም የኪነ ጥበብ ዘርፍ ባለሙያዎችና ለዚህ ራዕይ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል። 


ስለ ፌስቲቫሉ እና ውድድሩ ተጨማሪ ዝርዝር እና የተሟላ ማብራሪያ እዚህ ተያይዟል

የውድድሮቹ የተሳትፎ ቅጽ፣ አጠቃላይ መመሪያዎች እና ደንቦች

Related posts

November 4, 2023November 9, 2023 3rd Film Festival
የኢሰመኮ 3ኛ ዙር የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፎች እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ተራዘመ
October 3, 2023March 26, 2024 3rd Film Festival
3ኛው የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል:- የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልም ውድድሮች ተጀመረ
December 11, 2023December 20, 2023 3rd Film Festival
የኢሰመኮ ሦስተኛው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በይፋ ተጀመረ
December 5, 2022August 28, 2023 2nd Film Festival
የመጀመሪያው የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በጨረፍታ

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.