የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 24
ማንኛውም ሰው:-
- ሰብአዊ ክብሩ እና መልካም ስሙ የመከበር መብት አለው።
- የራሱን ስብእና ከሌሎች ዜጎች መብቶች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በነጻ የማሳደግ መብት አለው።
- በማንኛውም ስፍራ በሰብአዊነቱ ዕውቅና የማግኘት መብት አለው።
የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር፣ አንቀጽ 5
ማንኛውም ግለሰብ ተፈጥሯዊ የሆነውን የሰው ልጅ ክብር የማግኘት እና በሕግ ፊትም ዕውቅና የማግኘት መብት አለው።