Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

በንግድ እና ሰብአዊ መብቶች ላይ የተካሄደ የዐቅም ግንባታ ስልጠና

July 31, 2025July 31, 2025 Event Update

የንግድ ተቋማት ለሰብአዊ መብቶች መከበር ከፍተኛ ሚና አላቸው

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም (Danish Institute for Human Rights (DIHR)) እና ከኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጋር በመተባበር ንግድ እና ሰብአዊ መብቶች ላይ ያተኮረ የዐቅም ግንባታ ስልጠና ሐምሌ 18 ቀን 2017 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አካሂዷል። መድረኩ በንግድ ዐውድ ውስጥ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመለየት፣ ለመከላከል እና ለመቀነስ የሚያስችሉ የጥንቃቄ ሂደቶችን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች መመሪያ መርሖችን (United Nations Guiding Principles on Business and Human Rights) እንዲሁም በዝግጅት ሂደት ላይ የሚገኘውን የንግድ እና የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር በተመለከተ የንግዱን ማኅበረሰብ ግንዛቤ ለማሳደግ ያለመ ነው።

የስልጠናው ተሳታፊዎች

በስልጠናው አስመጪ እና ላኪዎች፣ አገልግሎት ሰጪዎች፣ አምራቾችን ጨምሮ በተለያዩ የንግድ ተግባራት ላይ የተሰማሩ ድርጀቶች እንዲሁም የፍትሕ ሚኒስቴር፣ የዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም እና የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ተወካዮች ተሳትፈዋል።

በስልጠናው የተባበሩት መንግሥታት የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች መመሪያ መርሖች መሠረታዊ ይዘቶችን አስመልክቶ በተለይም የንግድ ተቋማት ሰብአዊ መብቶችን የማክበር ኃላፊነትን በተመለከተ በዴንማርክ የሰብአዊ መብቶች ተቋም የምሥራቅ አፍሪካ ተወካይ ዶ/ር ኦጆት ሚሩ ገለጻ ተደርጓል። በመቀጠልም በኢትዮጵያ ያለው የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች ሁኔታ፣ ኢሰመኮ በንግድ ዐውድ ውስጥ የሰብአዊ መብቶችን መከበር ለማረጋገጥ የሚያደርጋቸው ጥረቶች፣ በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግሥታት መመሪያ መርሖችን በመተግበር የሚገኘው ጥቅም፣ የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር ምንነትና አስፈላጊነት እንዲሁም በዝግጀት ሂደቱ ታሳቢ ሊደረጉ የሚገቡ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ተሰጥቷል።

ሃዊ አስፋው፣ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ መብቶች ዳይሬክተር

በፍትሕ ሚኒስቴር መሪነት እየተከናወነ ያለው የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር ዝግጅት የደረሰበትን ደረጃ፣ የንግዱ ማኅበረሰብ ተሳትፎ እና በቀጣይም ከንግዱ ማኅበረሰቡ ጋር የሚካሄዱ ውይይቶችን አስመልክቶ በፍትሕ ሚኒስቴር የሰብአዊ መብቶች ዳይሬክተር አወል ሱልጣን ገለጻ አድርገዋል።

ብስራት በለጠ፣ የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር (በግራ) እና አወል ሱልጣን፣ በፍትሕ ሚኒስቴር የሰብአዊ መብቶች ዳይሬክተር

የኢትዮጵያ ንግድና የዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የቢዝነስ አመራር አካዳሚ ዳይሬክተር ብስራት በለጠ የንግድ ተቋማት በዓለም አቀፍ ደረጃ በተቀመጡ መስፈርቶችመሠረት ሰብአዊ መብቶችን በማክበር መሥራታቸው የገበያ ትስስርን ከማጠናከር፣ መልካም ስምን ከመገንባት እና ከመጠበቅ አንጻር ከፍተኛ ጥቅም ያለው መሆኑን ገልጸዋል።

ዶ/ር አብዲ ጅብሪል፣ የኢሰመኮ የሲቪል፣ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር

የኢሰመኮ የሲቪል፣ የፖለቲካ፤ የኢኮኖሚ እና የማኅበራዊ መብቶች ኮሚሽነር ዶ/ር አብዲ ጅብሪል የንግድ ድርጅቶች ለሰብአዊ መብቶች መከበር ከፍተኛ ሚና እንዳላቸው ሆኖም ግን ለሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች አስተዋጽዖ እንዳያደርጉ ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል።

Related posts

October 23, 2023October 27, 2023 Event Update
በብሔራዊ የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች የድርጊት መርኃ ግብር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
May 21, 2024May 22, 2024 Event Update
የንግድ እና የሰብአዊ መብቶች ብሔራዊ የድርጊት መርኃ ግብር ሥራ ማስጀመሪያ ምክክር መድረክ ተካሄደ
June 5, 2022October 6, 2022 Press Release
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) ሁሉን-አቀፍ የግምገማ መድረክ (Universal Periodic Review) ላይ የሲቪል ማኅበራት ሚና ማጎልበት
December 10, 2021August 26, 2023 EHRC Quote
ኢሰመድህ ከተ.መድ. የሰብአዊ መብቶች ከፍተኛ ኮሚሽነር የምስራቅ አፍሪካ ጽ/ቤት (UNOHCHR - EARO) ጋር በመተባበር ባዘጋጀው መርኃ ግብር ለኢሰመኮ ምስጋና አቀረበ

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.