በአፍሪካ ሕዝቦችና ሰዎች መብቶች ቻርተር የአፍሪካ አረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 14
አባል ሀገራት፦
- በተፈጥሮ አደጋዎች፣ በግጭት ወቅት፣ በጦርነት ወይም በእርስ በእርስ ግጭቶች ጊዜ ተጎጂዎችን ከአደጋ ለመጠበቅ በሚደረግ ጥረት፣ መልሶ በማቋቋም፣ በሰፈራ እና በሚወሰዱ ሌሎች እርምጃዎች ወቅት ለአረጋውያን ቅድሚያ የመስጠት ግዴታ አለባቸው።
- አረጋውያን በሁሉም ጊዜ ሰብአዊ እንክብካቤ፣ ጥበቃ እና ክብር እንዲያገኙ የማድረግ እና የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና ድጋፍ እና እንክብካቤ እንዳይነፈጋቸው የማድረግ ግዴታ አለባቸው።
የካምፖላ ኮንቬንሽን፣ አንቀጽ 9(2፣ሐ)
- አባል ሀገራት በሀገራቸው ውስጥ ለተፈናቀሉ ሰዎች በተለይም ልዩ ድጋፍ ለሚያሻቸው አረጋዉያንና ሌሎች ለጉዳት ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ልዩ ጥበቃና ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል።