ብሬል በትምህርት፣ ሐሳብን የመያዝና የመግለጽ ነጻነት፣ የመረጃ ተደራሽነት እንዲሁም በማኅበራዊ አካታችነት ለዐይነ ስውራን ወሳኝ የሆነ የኮሙኒኬሽን መንገድ ነው፡፡
በተ.መ.ድ. የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት መሠረት ፈራሚ ሀገራት፡-
- (ዐይነ ስውራን) የሕይወትና የማኅበራዊ እድገት ክህሎት እንዲያገኙ፣ ብሎም በማኅበረሰባቸው ውስጥ ሙሉና ውጤታማ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ለማስቻል የብሬል ትምህርትን የማመቻቸትና የማበረታታት ግዴታ አለባቸው፡፡ (አንቀጽ 24፣ 3(ሀ))
- በሕንጻዎችና ለሕዝብ ክፍት በሆኑ መገልገያዎች የመረጃና የአቅጣጫ ምልክቶችን በብሬል እና በቀላሉ ተነበው ለመረዳት በሚችሉ ጽሑፎች ለመግለጽ የሚያስችል ተገቢ እርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው፡፡ (አንቀጽ 9፣2(መ))