ዓለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 5(1) እና 9(1)
- አባል ሀገራት በአካል ጉዳተኝነት ላይ የተመሠረተ ማንኛውንም አድሏዊ ልዩነት ሊከለክሉ እና በሁሉም ሁኔታዎች ለአካል ጉዳተኞች እኩል እና ውጤታማ የሕግ ጥበቃ ሊያደርጉ ይገባል።
- አባል ሀገራት አካል ጉዳተኞች ራሳቸውን ችለው እንዲኖሩና በሁሉም የሕይወት ዘርፎች ሙሉ በሙሉ እንዲሳተፉ ለማስቻል ከሌሎች ጋር በእኩልነት የከበባያዊ፣ የመጓጓዣ፣ የመረጃና የተግባቦት ቴክኖሎጂዎችን እና ሥርዓቶችን ጨምሮ ተደራሽ እንዲሆኑላቸው ተገቢ እርምጃዎችን ሊወስዱ ይገባል። እንዲሁም በከተማም ሆነ በገጠር ለሕዝብ ክፍት የሆኑ አገልግሎቶች እና መገልገያዎችን ማግኘታቸውን ማረጋገጥ አለባቸው።