የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 18(2 እና 3)
- ማንኛውም ሰው በባርነት ወይም በግዴታ አገልጋይነት ሊያዝ አይችልም። ለማንኛውም ዓላማ በሰዉ የመነገድ ተግባር የተከለከለ ነው።
- ማንኛውም ሰው በኃይል ተገዶ ወይም ግዴታን ለማሟላት ማንኛውንም ሥራ እንዲሠራ ማድረግ የተከለከለ ነው።
የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 8
- በኃይል ተገዶ ወይም በግዳጅ ሥራዎችን እንዳያከናውን የተቀመጠው ክልከላ፤ የግዳጅ ሥራ ከእስራት ጋር እንደቅጣት በሚወሰንባቸው ሀገራት ውስጥ ሥልጣን ያለው ፍርድ ቤት የሰጠውን ከባድ የጉልበት ሥራን የማከናወን የቅጣት ውሳኔ ተፈጻሚ እንዳይሆን የሚከለክለው ተደርጎ መወሰድ የለበትም።