ሁሉንም ሰው ከአስገድዶ መሰወር ለመጠበቅ የወጣ መግለጫ፣ አንቀጽ 1 

  • ማንኛውም የአስገድዶ መሰወር ተግባር ሰብአዊ ክብርን የሚጥስ ድርጊት ነው። ይህ ተግባር የተባበሩት መንግሥታት ቻርተር ዐላማዎችን የሚጣረስ እንዲሁም በዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች መግለጫ እና በዘርፉ ባሉ ዓለም አቀፍ ሰነዶች ውስጥ የተደነገጉ እና ተጨማሪ ዕውቅና ያገኙ ሰብአዊ መብቶች እና መሠረታዊ ነጻነቶች ላይ የሚፈጸም ከባድ እና ግልጽ ጥሰት ተደርጎ ይወሰዳል። 

የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 28(1) 

  • ኢትዮጵያ ባጸደቀቻቸው ዓለም አቀፍ ስምምነቶች እና በሌሎች የኢትዮጵያ ሕጎች በሰው ልጅ ላይ የተፈጸሙ ወንጀሎች ተብለው የተወሰኑትን ወንጀሎች፣ የሰው ዘር የማጥፋት፣ ያለፍርድ የሞት ቅጣት እርምጃ የመውሰድ፣ በአስገዳጅ ሰውን የመሰወር፣ ወይም ኢ-ሰብአዊ የድብደባ ድርጊቶችን በፈጸሙ ሰዎች ላይ ክስ ማቅረብ በይርጋ አይታገድም። በሕግ አውጪው ክፍልም ሆነ በማንኛውም የመንግሥት አካል ውሳኔዎች በምሕረት ወይም በይቅርታ አይታለፍም።