ማንኛውም ሰው ዕረፍትና የመዝናኛ ጊዜ የማግኘት መብት አለው፤ በቀን ለተወሰኑ ሰዓቶች ብቻ የመሥራትና በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጥ ዕረፍት የማግኘት መብትም አለው፡፡ (የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፋዊ መግለጫ፣ አንቀጽ 24)
ለሠራተኞች መብቶች ጥበቃ የሚሰጠው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. ሕገ መንግሥት አንቀጽ 42(2) እንደሚያስቀምጠው ሠራተኞች፡-
- በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት ዕረፍት፣
- የመዝናኛ ጊዜ፣
- በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀኖች፣
- ደሞዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም
- ጤናማና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብቶች አሏቸው፡፡
Photo credit: gordontour