በአፍሪካ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ አስመልክቶ የተደረገው የአፍሪካ ሕብረት ስምምነት (ካምፓላ ስምምነት)፣ አንቀጽ 9(2(ለ))
አባል ሀገራት ለሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ ማድረግ እስከሚቻለው እና በተቻለ መጠን ባለመዘግየት ምግብ፣ ውሃ፣ መጠለያ፣ ሕክምና እና ሌሎች የጤና አገልግሎቶች፣ የአካባቢ ጽዳትና የግል ንጽሕና፣ ትምህርት እና ሌሎች አስፈላጊ ማኅበራዊ አገልግሎቶችን ያካተተ በቂ የሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እንደአስፈላጊነቱም እነዚህን ድጋፎች ተፈናቃዮችን ለተቀበለው ማኅበረሰብ እንዲሁም ለአካባቢው ነዋሪዎች ማድረስ ይገባል፡፡
የተ.መ.ድ. የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች መመሪያ መርሖች፣ መርሕ 3(ለ)
የተፈናቀሉ ሰዎች ከመንግሥት አካላት ጥበቃ እና ሰብአዊ ድጋፍ የመጠየቅ እና የማግኘት መብት አላቸው። ይህን ጥያቄ በማቅረባቸው ሊከሰሱ ወይም ሊቀጡ አይገባም።