የሕፃናት መብቶች ስምምነት፣ አንቀጽ 12 (1) እና (2) 

  • አባል ሀገራት ሐሳብ ለማመንጨት ችሎታ ያለው ማንኛውም ሕፃን በሚመለከተው ጉዳይ ሁሉ ሐሳቡን በነጻነት የመግለጽ መብቱን ያረጋግጣሉ። ሕፃኑ የሚያቀርበው ሐሳብ ዕድሜውና በአእምሮ የመብሰል ሁኔታው እየታየ ተገቢው ክብደት ይሰጠዋል። 
  • ለዚህ ዓላማ ሲባል በተለይ ሕፃኑን የሚመለከት ጉዳይ በዳኝነት ወይም በአስተዳደር አካል በሚታይበት ጊዜ ከሀገሩ የሥነ-ሥርዓት ሕግ ጋር በተጣጣመ ሁኔታ በራሱ በቀጥታ ወይም በእንደራሴ ወይም አግባብ ባለው አካል በኩል የመሰማት ዕድል ይሰጠዋል።