ሴቶች የማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና የባሕል መብቶቻቸው በሕግ ጥበቃ ተደርጎላቸዋል፡፡
በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት አንቀጽ 13
የስምምነቱ አባል ሀገራት በሌሎች የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ መስኮች በሴቶች ላይ የሚደረጉ አድሎአዊ ልዩነቶችን በማስወገድ ሴቶች ከወንዶች እኩል የኢኮኖሚና ማኅበራዊ መብቶቻቸው ተጠቃሚ እንዲሆኑ፤ በተለይም
ሀ) የቤተሰብ ጥቅማ ጥቅም የማግኘት መብት፤
ለ) በንብረት ማስያዥያነት የሚገኝ ብድርን ጨምሮ የባንክ ብድር እና ከሌሎች ምንጮች የገንዘብ ብድር የማግኘት መብት፤
ሐ) በመዝናኛ፣ በስፖርትና በሌሎች ባሕላዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የመሳተፍ መብትን
ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ተገቢ ርምጃዎችን መውሰድ አለባቸው፡፡
Photo Credit: Pete Lewis/Department for International Development