በሴቶች ላይ የሚደረግ ማንኛውንም አድሎአዊ ልዩነት ለማስወገድ የተደረገ ስምምነት፣ አንቀጽ 12 (1)
- አባል ሀገራት የወንዶች እና የሴቶች እኩልነትን መሠረት በማድረግ የቤተሰብ ምጣኔን ጨምሮ የጤና ጥበቃ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ በጤና ጥበቃ ዘርፍ በሴቶች ላይ የሚደርሰውን አድልዎ ለማስወገድ ተገቢውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ።
የአፍሪካ የሰዎችና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የሴቶች መብቶች ፕሮቶኮል (ማፑቶ ፕሮቶኮል)፣ አንቀጽ 14 (2) (ሀ)
- አባል ሀገራት ለሴቶች በተለይም በገጠር ለሚገኙ የመረጃ፣ የትምህርት እና የግንኙነት መርኃ ግብሮችን ጨምሮ በቂ፣ ተመጣጣኝ እና ተደራሽ የጤና አገልግሎቶችን ለመስጠት አስፈላጊውን እርምጃ ሁሉ ይወስዳሉ።