የአፍሪካ ሕብረት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ (ክፍል፣ 19)
ጠቅለል ባለ መልኩ፣ የሽግግር ፍትሕ አንድ ማኅበረሰብ ለደረሰበት መጠነ ሰፊ ጉዳቶች፣ ወይም ለደረሱ ቆየት ያሉ/ታሪካዊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና ጥልቅ ክፍፍሎች እና መራራቅ/ኢ_እኩልነትን ለማረቅ እና መፍትሔ/እልባት ለመስጠት የሚካሄዱ መደበኛ ወይም መደበኛ ያልሆኑ ሂደቶች እና መዋቅሮች ማለት ነው።
ሁሉን አቀፍ የሽግግር ፍትሕ እርስ በእርሳቸው የሚደጋገፉና የሚዛመዱ አራት ዋና ዋና ሂደቶችን የያዘ ነው፦
- እውነትን ማረጋገጥና ይፋ ማድረግ፣
- ተጠያቂነት፣
- ለተጎጂዎች ምሉዕ ካሳና መቋቋም ማስገኘት እንዲሁም፣
- የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ዳግም እንደማይፈጸሙ ተጨባጭ ማረጋገጫ ማቅረብ።