Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

የሽግግር ፍትሕ እና ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች

April 1, 2024April 1, 2024 Explainer

ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶችን ያማከለ የሽግግር ፍትሕ ምንድነው? በሽግግር ፍትሕ ሂደት ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች እንዴት መካተት ይችላሉ?

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Print

ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶችን ያማከለ የሽግግር ፍትሕ ምንድነው? 

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተ.መ.ድ.) የሽግግር ፍትሕ መመሪያ ማስታወሻ እና የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ እንዳስቀመጡት፣ የሽግግር ፍትሕ ማለት  አንድ ማኅበረሰብ ያለፉ መጠነ ሰፊ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን፣ ክፍፍሎችን እና አለመመጣጠኖችን ለማስወገድ፣ ፍትሕን ለማስፈን እና ዕርቅን ለማውረድ፣ ለደኅንነትም ሆነ ለዴሞክራሲያዊ እና ማኅበራዊ-ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ሥርዓት ግንባታ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር የሚወስዷቸው የተለያዩ (መደበኛ እና ባህላዊ/መደበኛ ያልሆኑ) የፖሊሲ እርምጃዎችን እና ተቋማዊ አሠራሮች የሚያመለክት ሂደት ነው። የሽግግር ፍትሕ አጠቃላይ ዓላማ ላለፉ በደሎች እና የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተገቢ ምላሽ በመስጠት ዘላቂ ሰላም እና ፍትሕ ማምጣት እንዲሁም ወደ ዕርቅ ማምራት ነው። ይህን ለማሳካት አራት (4) እርስ በርስ የተያያዙ እና የሚደጋገፉ መሠረታዊ ይዘቶችን/ስልቶችን የሚያካትት ነው። ይህም እውነትን ማፈላለግ፣ ተጠያቂነትን ማስፈን፣ ለተጎጂዎች ማካካሻ መስጠት፣ እና ጉዳቶች/ጥሰቶች እንዳይደገሙ ዋስትና ለመስጠት የሚወሰዱ ተቋማዊና ሌሎች ማሻሻያዎች ማድረግን ጨምሮ በማኅበረሰባዊ እና ባህላዊ ዘርፎች የሚወሰዱ እርምጃዎችን መተግበር ያካትታል (የተ.መ.ድ. የሽግግር ፍትሕ መመሪያ ማስታወሻ፣ መርሕ 8) ።

ምንም እንኳን በኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ላይ የሚፈጸሙ መዋቅራዊ እና ስልታዊ ጥሰቶች ለግጭቶች ምክንያት የሚሆኑና በግጭት ወቅት በሚፈጸሙ ድርጊቶችም መጠነ ሰፊ የኢኮኖሚያዊ እና የማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶች የሚደርሱ ቢሆንም አብዛኛውን ጊዜ ከግጭት በኋላ በሚኖሩ የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች የኢኮኖሚያዊ እና የማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን ያለማካተትና በሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ጥሰቶች ብቻ ላይ የማተኮር አካሄድ ይስተዋልባቸዋል።

ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶችን ከሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች የተለዩ አድርጎ የመመልከት የቆየ አዝማሚያ መኖሩና፣ የሽግግር ፍትሕ አሠራር እና ፅንሰ ሐሳብ ከመዋቅራዊ የፍትሕ መጓደሎች ይልቅ አትኩሮቱን በዋናነት  የግለሰብ ተጠያቂነት ማስፈን ላይ ባደረገው ዓለም አቀፍ የወንጀል ሕግ በከፍተኛ ሁኔታ መቃኘቱ ለክፍተቱ እንደ ምክንያት ይጠቀሳሉ። ይህ የቆየ የሽግግር ፍትሕ እሳቤ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሁሉን አቀፍ በሆነ አረዳድ እየተተካ የመጣ ሲሆን፣ በተለይም በተለምዶ የአረብ ሀገራት አብዮት በመባል የሚታወቀው እና በዋናነት በቱኒዝያ እና በግብጽ ከተካሄዱት አብዮቶች በኋላ የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲሁም የማኅበራዊ ፍትሕ ጉዳዮችን ማካተት እንደሚኖርባቸው ታምኖበታል።

ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶችን ያማከለ የሽግግር ፍትሕ ይህን ሁሉን አቀፍ አረዳድ የሚከተልና በግጭት ለደረሱ የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ጥሰቶች መፍትሔ ከማፈላለግ ባለፈ የሽግግር ፍትሕ ሂደቶች ለግጭቶች ምክንያት/አባባሽ ሆነው የቆዩ መዋቅራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጉዳዮችን ጨምሮ በግጭት ወቅት ለደረሱ ሁሉም የመብት ጥሰቶች ምላሽ በሚሰጥ መልኩ ሊተገበሩ ይገባል የሚለውን አስተሳሰብ የሚወክል ነው። 

በሽግግር ፍትሕ ሂደት ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች እንዴት መካተት ይችላሉ?

በተ.መ.ድ. ዋና ጸሐፊ የወጣው የመመሪያ ማስታወሻ እንደተገለጸው በሽግግር ፍትሕ ወቅት ተግባራዊ የሚደረጉ አሠራሮች የግጭት መንስኤዎችን ከግምት ውስጥ የሚያስገቡ እና ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶችን ጨምሮ ለደረሱ የመብት ጥሰቶች ሁሉን አቀፍ እና በተቀናጀ መልኩ መፍትሔ ለመስጠት ያለሙ መሆን ይገባቸዋል። ስለሆነም ከዚህ በመቀጠል ባለው ክፍል ተግባራዊ የሚደረጉ የሽግግር ፍትሕ ስልቶች (የወንጀል ተጠያቂነት፣ እውነትን ማፈላለግ፣ ለተጎጂዎች ማካካሻ መስጠት፣ እና ጉዳቶች/ጥሰቶች እንዳይደገሙ ዋስትና መስጠት) ለኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶች ምላሽ ከመስጠት አንጻር ሊኖራቸው የሚችለውን ሚና እንመለከታለን።

1. የወንጀል ተጠያቂነት

የተ.መ.ድ. መመሪያ በሽግግር ፍትሕ ሂደት የኢኮኖሚያዊ እና የማኅበራዊ መብቶች እንዲሁም የሲቪል እና የፖለቲካ መብቶች ጥሰት ሆነው የሚቆጠሩ ድርጊቶችን በሀገር አቀፍ ወይም በዓለም አቀፍ ሕግጋት መሠረት መመርመር፣ ክስ ማቅረብ እና መቅጣት እንደሚገባ ያሳስባል።

በመሆኑም በሽግግር ፍትሕ የጊዜ ወሰን በሚሸፈኑ ጊዜያት በግጭትም ሆነ ከግጭት ውጪ በሆነ መልኩ የተፈጠሩ ከፍተኛ የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን ደረጃዎችን በማውጣት አመልካች በሆነ መንገድ (symbolic) የክስ ሂደት አካል እንዲሆኑ ማድረግ ያስፈልጋል። ይህን በሁለት መልኩ ማድረግ ይቻላል። አንደኛ ከግጭት ውጪ ባለው አውድ በሙስና እንዲሁም በሌሎች ቀጥተኛ ድርጊቶች ለምሳሌ አስገድዶ በማስነሳት እና በሌሎች ሁኔታ የማኅበረሰቡ ኑሮ የተመሠረተባቸውን የተፈጥሮ ሀብቶች በማሳጣት ለደረሱ ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ተጠያቂነትን ማረጋገጥ ነው።  ሁለተኛ በግጭት ወቅት የደረሱ የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን በተለየ ሁኔታ መመርመር እና መቅጣት ነው። ለምሳሌ መጠነ ሰፊ የመኖሪያ ቤትና የንብረት ውድመት/ዝርፊያ፣ በግዳጅ ማፈናቀል፣ ሰብአዊ ድጋፍ እንዳይደርስ መከልከል፣ ለማኅበረሰቡ ሕልውና አስፈላጊ የሆኑ መሠረተ ልማቶችን ማውደም እና ሌሎች ተመሳሳይ ድርጊቶች እንደነገሩ ሁኔታ ዓለም አቀፍ ወንጀሎች (በሰብአዊነት ላይ የሚፈጸም ወንጀል፣ የጦር ወንጀል እንዲሁም የዘር ማጥፋት ወንጀል) ሆነው ሊወሰዱ የሚችሉ እንደመሆናቸው እንደዚህ ያሉ ጥሰቶችን አለመመርመር፣ ክስ አለመመሥረት እና አለመቅጣት ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎችም ሆነ ከዓለም አቀፍ የሰብአዊነት እና የወንጀል ሕግጋት አንጻር ተቀባይነት አይኖረውም።

 ዓለም አቀፍ ወንጀሎችን የሚያንጸባርቁ የወንጀል ሕግ ድንጋጌዎችን ማውጣት እንዲሁም ያለመከሰስ እና የይርጋ መብቶችን የሚመለከቱ ደንቦች ተያያዥ ጉዳዮችን ለመመርመር እና ክስ ለማቅረብ እንቅፋት በማይሆኑ መልኩ ማሻሻል የሽግግር ፍትሕ ሂደት የስኬት አመላካቾች እንደሆኑ የአፍሪካ ኅብረት የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ ማዕቀፍ ያስቀምጣል።

2. የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽኖች

ሀገራት የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽኖችን ሲያቋቁሙ የኢኮኖሚያዊ እና የማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲመረምሩ እና የማስተካከያ ምክረ ሐሳቦችን እንዲያቀርቡ በሚያስችል መልኩ ማዋቀር እንደሚገባቸው የተ.መ.ድ. የሽግግር ፍትሕ መመሪያ ማስታወሻ ያስቀምጣል።

በሽግግር ፍትሕ ወቅት የሚቋቋሙ የእውነት አፈላላጊ ኮሚሽኖች ከሚያከናውኗቸው ተግባራት አንዱ የግጭቶች መሠረታዊ ምክንያቶች እንዲሁም በግጭቱ የደረሱ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን መለየት፣ ይፋ ማውጣት እና የመፍትሔ ምክረ ሐሳቦችን ማቅረብ ነው። ይህም ለግጭቶች መሠረታዊ ምክንያት የሆኑ መዋቅራዊ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲሁም በግጭቱ ወቅት የደረሱ የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን ለመለየት፣ ለመሰነድ እና መፍትሔ ለማመላከት ምቹ ያደርጋቸዋል። የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን በእውነት የማፈላለግ እና ይፋ የማውጣት ተግባር አካል አለማድረግ ያለፉ ሁነቶች በተሟላ መልኩ እንዳይሰነዱ ከማድረግ አልፎም የሚወሰዱ የማስተካከያ እርምጃዎች ውጤታማነት ላይ አሎታዊ ተጽዕኖ ያሳድራል።

ለግጭት ምክንያት የሆኑ መዋቅራዊ ጉዳዮችን እና በግጭት ወቅት የተፈጸሙ የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን በእውነት የማፈላለግ ሂደቶች የማካተት አሠራር በሌሎች በሽግግር ፍትሕ ወይም በእውነት ማፈላለግ ሂደት ውስጥ ባለፉ ሀገራት ተሞክሮዎች አሉ። በተለይም የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን በጥልቀት በመመርመርና በዝርዝር በመሰነድ ረገድ የምሥራቅ ቲሞር የእውነት እና ዕርቅ አፈላላጊ ኮሚሽን ልምድን በዋናነት ማንሳት የሚቻል ሲሆን በላይቤሪያ እና በሴራሊዮን የተቋቋሙ የእውነት እና የዕርቅ ኮሚሽኖችም የኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን በእውነት የማፈላለግ ተግባር ማካተታቸውን መመልከት ይቻላል።

3. ማካካሻ

ማካካሻ ተጎጂዎችን ወደነበሩበት መመለስ፣ ካሳ፣ ማገገሚያ፣ እርካታ እና ያለመድገም ዋስትና ለማረጋገጥ የሚረዱ እርምጃዎችን የሚያካትት ዘርፈ-ብዙ ጉዳዮችን የያዘ የሽግግር ፍትሕ ስልት ነው። ከዚህ ጋር በተያያዘ በግጭትም ሆነ ከግጭት ውጪ በደረሱ ከፍተኛ የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶች ተጎጂ ለሆኑ ግለሰቦች እና ማኅበረሰቦች የሚሰጡ ማካካሻዎች በተቻለ መጠን የተጎጂዎችን ፍላጎት መሠረት ባደረገ መልኩ ወደ ቀድሞ መኖሪያ ስፍራቸው መመለስን/በሌሎች ቦታዎች ማስፈርን፤ አላግባብ ያጡትን ንብረት፣ ቤት፣ መሬት፤ ሥራ እንዲያገኙ ማድረግን፣ የግጭት ጉዳቶችን ለመቋቋም የሚያስችሉ ሥነ ልቦናዊ ድጋፎችን መስጠትን፤ በግጭቱ የታጡ የትምህርት ጊዜያትን የሚያካክስ የትምህርት ሥርዓት መተግበርን፣ እንደ ሆስፒታል እና ትምህርት ቤት ያሉ ጉዳት የደረሰባቸው የሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተቋማትን መልሶ መገንባትን ባካተተ መልኩ ሊተገበሩ ይገባል። በተጨማሪም ተጎጂዎች ያሉባቸውን አንገብጋቢ እና አስቸኳይ ችግሮች በተወሰነ መልኩ ለመቅረፍ ይረዳ ዘንድ የተሟላ የማካካሻ ሥርዓት እስኪተገበር ድረሰ እንደ ምግብ፣ ውሃ፣ ንጽሕና መጠበቂያ፣ መጠለያ እና የጤና አገልግሎት ያሉ መሠረታዊ አገልግሎቶችን ተደራሽ ለማድረግ ጣልቃ-ገብ የማካካሻ ወይም የድጋፍ ተግባራትን መቀየስ ያስፈልጋል።

4. ጥሰቶች እንዳይደገሙ ዋስትና ለመስጠት የሚወሰዱ እርምጃዎች (ተቋማዊ፣ የሕግና ሌሎች ማሻሻያዎች)

በሽግግር ፍትሕ ጥሰቶች እንዳይደገሙ ዋስትና ለመስጠት የሚወሰዱ እርምጃዎች ለምሳሌ ተቋማዊና የሕግ ማሻሻያዎች ለግጭቶች መንስኤ የሆኑ መዋቅራዊ የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲሁም በግጭቱ ወቅት የደረሱ የኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች ጥሰቶችን እንዲፈጸሙ ያስቻሉ የሕግ ማዕቀፎች እና አሠራሮችን በተገቢ መልክ መለወጥ እና ጥሰቶች እንዳይደገሙ ማድረግን ታሳቢ ሊያደርጉ ይገባል። ለዚህም በተለይም ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች በዝርዝር ሕገ መንግሥታዊ ጥበቃ እንዲሰጣቸው ማድረግን፤ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ መብቶች በፍርድ ቤት ዳኝነት የሚያገኙ ጉዳዮች (Justiciable) እንደሆኑ በግልጽ ዕውቅና መስጠትን፤  የመሬት እና ሌሎች የተፈጥሮ ሀብቶችን እኩል እና ፍትሐዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥን፣ ሙስናን መከላከልን፣ በታሪክ የተገለሉ እና በግጭቱ በተለየ ሁኔታ የተጎዱ ማኅበረሰቦችን የልዩ ድጋፍ ተጠቃሚ ማድረግን ጨምሮ ሌሎች የግጭት ምክንያት ሆነው የቆዩ ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ጉዳዮችን በሕገ መንግሥት ወይም በሌሎች ሕጎች እንዲሁም ተቋማዊ ማሻሻያዎች እንዲፈቱ የሚያስችል ሂደት መከተል ያስፈልጋል።

Related posts

April 24, 2023September 30, 2023 Explainer
በሽግግር ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ የአረጋውያን እና አካል ጉዳተኞች ተሳትፎ እና ተካታችነት
October 23, 2023October 27, 2023 Event Update
በብሔራዊ የንግድ እና ሰብአዊ መብቶች የድርጊት መርኃ ግብር ዙሪያ ከባለድርሻ አካላት ጋር የተካሄደ ውይይት
March 24, 2022August 28, 2023 Event Update
በኢትዮጵያ እውነትን የማወቅ መብትን ጨምሮ የሽግግር ፍትሕ ላይ እየተካሄደ ያለ አውደ ጥናት
June 16, 2022October 6, 2022 Public Statement
ልዩ ትኩረት በአረጋውያን ላይ ለሚደርስ ጥቃት እና ጉዳት

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.