የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፋዊ መግለጫ፣ አንቀጽ 17
- ማንኛውም ሰው ብቻውንም ሆነ ከሌሎች ጋር በመተባበር የንብረት ባለቤት የመሆን መብት አለው።
- ማንም ሰው በዘፈቀደ ንብረቱን እንዲያጣ አይደረግም::
የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 40
- ማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ የግል ንብረት ባለቤት መሆኑ ይከበርለታል።
- ይሕ መብት የሕዝብን ጥቅም ለመጠበቅ በሌላ ሁኔታ በሕግ እስካልተወሰነ ድረስ ንብረት የመያዝና በንብረት የመጠቀም፤ ወይም የሌሎችን ዜጎች መብቶች እስካልተቃረነ ድረስ ንብረትን የመሸጥ፣ የማውረስ ወይም በሌላ መንገድ የማስተላለፍ መብቶችን ያካትታል።