የአፍሪካ የሰዎች እና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የአረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 7
አባል ሀገራት፦
- ከሥራ ገበታቸው የሚሰናበቱ አረጋውያን በቂ የጡረታ አበል እና ሌሎች የማኅበራዊ ዋስትና ዓይነቶች እንዲኖሯቸው የሚያረጋግጡ ፖሊሲዎችን እና ሕጎችን ማውጣት፤
- ለየትኛውም ዓይነት የማኅበራዊ ዋስትና አገልግሎት አስተዋጾ ለማድረግ ዕድል ላላገኙ አረጋያን የገቢ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚያስችል ሁሉን አቀፍ የማኅበራዊ ጥበቃ አገልግሎት ሥርዓት መዘርጋቱን ማረጋገጥ፤
- የጡረታ አበል የማግኘት ሂደቶች እና ሥነ ሥርዓቶች ያልተማከለ፣ ቀላል እና አክብሮት የታከለባቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ፤
- ግለሰቦች በአረጋዊነት ጊዜ ገቢ እንዲኖራቸው ለማስቻል የሕግ ማውጣት እና ሌሎች እርምጃዎችን መውሰድ እና
- አረጋውያን ከመንግሥት አገልግሎት ሰጪዎች አገልግሎቶችን የማግኘት መብቶቻቸውን የሚያመቻቹ የሕግ እና ሌሎች እርምጃዎች የመውሰድ ግዴታ አለባቸው።