የተባበሩት መንግሥታት የአረጋውያን መርሖች፣ መርሕ 10

  • አረጋውያን በማንኛውም መጠለያ፣ መንከባከቢያ ወይም የድጋፍ ማእከል ውስጥ በሚኖሩበት ጊዜ ሰብአዊ መብቶቻቸው እና መሠረታዊ ነጻነቶቻቸው ሊረጋገጡላቸው ይገባል፤ይህም ስለሚደረግላቸው እንክብካቤ እና ስለሕይወታቸው ሁኔታ የመወሰን መብታቸውን እንዲሁም ክብራቸውን፣ እምነታቸውን፣ ፍላጎቶቻቸውን እና ግላዊ ሕይወታቸውን ሙሉ በሙሉ ማክበርን ይጨምራል።

አፍሪካ የሰዎች እና ሕዝቦች መብቶች ቻርተር የአረጋውያን መብቶች ፕሮቶኮል፣ አንቀጽ 10 (2) እና (3)

  • አባል ሀገራት፦
    • የቤተሰብ እና የኅብረተሰቡ በዕድሜ የገፉ የቤተሰብ አባላትን እንክብካቤ እንዲጎለብት ባህላዊ የድጋፍ ሥርዓቶችን መለየት፣ ማስፋፋት እና ማጠናከር፤ እንዲሁም
    • በአገልግሎት አሰጣጥ ወቅትም ቅድሚያ የሚስተናገዱ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው።