የኢኮኖሚ፣ ማኅበራዊ እና ባህላዊ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃል ኪዳን፣ አንቀጽ 7
ተዋዋይ ሀገራት እያንዳንዱ ሰው ከአደጋ ነጻ የሆነና ጤናማ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል ፍትሐዊ እና አመቺ የሥራ ሁኔታ የማግኘት መብት ያለው መሆኑን እውቅና ሰጥተዋል።
የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት፣ አንቀጽ 42(2)
ሠራተኞች በአግባቡ የተወሰነ የሥራ ሰዓት፣ ዕረፍት፣ የመዝናኛ ጊዜ፣ በየጊዜው ከክፍያ ጋር የሚሰጡ የዕረፍት ቀናት፣ ደመወዝ የሚከፈልባቸው የሕዝብ በዓላት እንዲሁም ጤናማ እና አደጋ የማያደርስ የሥራ አካባቢ የማግኘት መብት አላቸው።