የሰብአዊ መብቶች ዓለም አቀፋዊ መግለጫ፣ አንቀጽ 14
ማንም ሰው ከጥቃት ለማምለጥና በሌሎች ሀገራት ጥገኛ ሆኖ ለመኖር የመጠየቅ መብት አለው፡፡
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አፍሪካ ህብረት) ስደተኞች ኮንቬንሽን፣ አንቀጽ 2
የአፍሪካ አንድነት ድርጅት (አፍሪካ ህብረት) አባል ሀገራት በአሳማኝ ምክንያቶች ወደ ትውልድ ሀገራቸው መመለስ የማይችሉ ወይም ፍቃደኛ ያልሆኑ ስደተኞችን ለመቀበል እና ማቆያ ለማመቻቸት ከሕጎቻቸው ጋር በተጣጣመ መልኩ የተቻላቸውን ሁሉ ጥረት ማድረግ አለባቸው፡፡