የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 37 (1) እና (2)
- ማንኛውም ሰው በፍርድ ሊወሰን የሚገባውን ጉዳይ ለፍርድ ቤት ወይም ለሌላ በሕግ የዳኝነት ሥልጣን ለተሰጠው አካል የማቅረብና ውሳኔ ወይም ፍርድ የማግኘት መብት አለው።
- ይህን ውሳኔ ወይም ፍርድ፦
ሀ) ማንኛውም ማኅበር የአባላቱን የጋራ ወይም የግል ጥቅም በመወከል፤
ለ) ማንኛውንም ቡድን ወይም ተመሳሳይ ጥቅም ያላቸውን ሰዎች የሚወክል ግለሰብ ወይም የቡድን አባል የመጠየቅ እና የማግኘት መብት አለው።