Skip to content
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Ethiopian Human Rights Commission – EHRC
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
        • Regions

          EHRC is an independent federal institution tasked with the promotion and protection of human rights in Ethiopia.

        • Addis Ababa
        • Afar
        • Amhara
        • Benishangul Gumuz
        • Gambella
        • Oromia
        • Somali
        • Tigray
        • Central Ethiopia
        • Dire Dawa
        • Harari
        • Sidama
        • South Ethiopia
        • South West Ethiopia Peoples'
  • Areas of Work
        • Areas of Work

          We are an independent national human rights institution tasked with the promotion & protection of human rights in Ethiopia.

        • Economic, Social & Cultural Rights
        • Civil & Political Rights
        • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
        • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
        • Women’s & Children’s Rights
        • Human Rights Education
        • Human Rights Monitoring & Investigation
        • Human Rights Film Festival
        • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
 
Ethiopian Human Rights Commission – EHRCEthiopian Human Rights Commission – EHRC

3ኛው የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል:- የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልም ውድድሮች ተጀመረ

October 3, 2023March 26, 2024 3rd Film Festival, Press Release

የ2016 ዓ.ም. የኢሰመኮ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ላይ የሚያተኩር ሲሆን፣ ኅዳር 30 ቀን የሚውለው የዘንድሮ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀን ዓለም አቀፉን የሰብአዊ መብቶች መግለጫ 75ኛ ዓመት የሚታሰብበት ዝግጅት በመሆኑ ልዩ ያደርገዋል፤ ሁሉም ሰው በውድድሩ እንዲሳተፍ እና ሂደቱን እንዲከታተል ተጋብዟል

Twitter Facebook Telegram Email Whatsapp Download Print

በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አዘጋጅነት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ በየዓመቱ በሚካሄደው የዘንድሮው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል ለዕይታ የሚቀርቡ አጫጭር ፊልሞች እና የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ውድድር እንደተዘጋጀ እና ውድድሩ በኢሰመኮ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት አሳሳቢ ተብለው በተለዩት በሕይወት የመኖር መብት እና በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት በማግኘት መብት ላይ የሚያተኩር መሆኑን ከነሐሴ ወር 2015 ዓ.ም. ጀምሮ ሲገልጽ መቆየቱ ይታወቃል። ውድድሩ በመስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም. በይፋ የተጀመረ ሲሆን፣ እስከ ጥቅምት 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ለተወዳዳሪዎች ክፍት ሆኖ የሚቆይ ይሆናል።

ይህ ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ በኢሰመኮ አዘጋጅነት የሚካሄደው የፊልም ፌስቲቫል “ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን” ማየት የሚለውን የኢሰመኮ ራዕይ ለማሳካት ኪነጥበብ ያለውን አስተዋጽዖ፣ እንዲሁም በሁለቱ ዘርፎች መካከል ያለውን ትስስር የሚያስታውስ ነው። ይህንን ውድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት የኪነጥበብ ዘርፎች በማዘጋጀት፣ ፌስቲቫሉ በየዓመቱ ለዕይታ የሚያቀርባቸውን የኪነጥበብ ሥራዎች፣ የሚያሳትፋቸውን የኪነ ጥበብ ዘርፎች፣ የዝግጅቱን ጥራት፣ የሚካሄድባቸውን አካባቢዎች እና ቦታዎች፣ ታዳሚዎችን በብዛት እና ለሰብአዊ መብቶች በሚያደርጉት አስተዋጽዖ ብዝኃነት፣ እንዲሁም በሚያካትታቸው የቋንቋዎች እና የማኅበረሰብ ክፍሎች ብዝኃነት እና በመሳሰሉት መስፈርቶች ሁሉ በየጊዜው እድገት በማሳየት በውድድር ለሚሳተፉ የኪነጥበብ ባለሞያዎችም ሆነ በሰብአዊ መብቶች ዘርፎች ለሚሠሩ የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ ተቋማት ከፍተኛ ጠቀሜታ ያለው መድረክ ለማድረግ ያለመ ነው።

በፎቶግራፍ ውድድሩ ጀማሪዎች (አማተር) ወይም ባለሞያዎች መሳተፍ የሚችሉ ሲሆን፣ ትኩረቱን በቂ የሆነ መኖርያ ቤት የማግኘት መብት ላይ ያደረገ ነው። የአጫጭር ፊልም ውድድሩ ደግሞ በሕይወት የመኖር መብት ላይ ትኩረት በማድረግ፣ በአንድ በኩል በተንቀሳቃሽ ስልክ (ሞባይል) የተቀረጸ እና ከ9 ደቂቃዎች ያልበለጠ አጭር ፊልም ዘርፍ ጀማሪዎችንም ባለሞያዎችንም የሚያሳትፍ፣ በሌላ በኩል በተለይ ባለሞያዎች እንዲሳተፉበት የታለመ እና ከ25 ደቂቃዎች ያልበለጠ ዘጋቢም ሆነ ልብ ወለድ ትረካ ፊልም የሚያወዳድር ነው። 

በሁለቱም የኪነጥበብ ዘርፎች ለሁሉም ተሳታፊዎች ልዩ ልዩ የዕውቅና እና የሽልማት ዐይነቶች የተዘጋጁ ሲሆን፣ በተጨማሪም በፎቶግራፍ ውድድር በተለይም ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለሚወጡ እንደየቅደም ተከተላቸው 40 ሺህ፣ 30 ሺህ እና 20 ሺህ ብር፣ ለሞባይል ፊልም ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ አሸናፊዎች 50 ሺህ፣ 40 ሺህ እና 30 ሺህ ብር እንዲሁም፣ ለአጭር ዘጋቢ ወይም ልብወለድ ፊልም ሥራ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ለሚወጡ 150 ሺህ፣ 120 ሺህ እና 100 ሺህ ብር ሽልማት ተዘጋጅቷል። (ስለ ውድድሩ የተሟላ መረጃ እዚህ ይገኛል)

ውድድሩ ተሳታፊዎች በቂ ስለሆነ የመኖሪያ ቤት የማግኘት መብት እና በሕይወት የመኖር መብት ትርጉም የተለያዩ ጥያቄዎችን የሚያጭሩ፣ ሐሳብ የሚሰጡ፣ የመብቱ መከበር ወይም መጣስ በተጨባጭ ምን እንደሚመስል የሚገልጹ እና ለማሰላሰል የሚጋብዙ የኪነጥበብ ሥራዎች የሚያቀርቡበት ይሆናል። ለውድድር የሚቀርቡ የኪነጥበብ ሥራዎች በሕይወት የመኖር መብት ወይም በቂ የሆነ መኖሪያ ቤት የማግኘት መብት ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ የሚጠበቁ ቢሆንም፣ ልዩ ትኩረት የሚሹ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ማለትም ሕፃናትን እና ታዳጊዎችን፣ ሴቶችን፣ አረጋውያንን፣ አካል ጉዳተኞችን፣ ሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን እና ስደተኞችን ለሚያካትቱ የገንዘብን ጨምሮ ልዩ ልዩ ማበረታቻዎች ተዘጋጅተዋል።

በሁለቱም ዘርፎች ማንኛውም ግለሰብ መሳተፍ እንዲችል ቀለል ያሉ የቴክኒክ መስፈርቶች የተቀመጡ ሲሆን፣ ውድድሩ መንግሥታዊ እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የሚዲያ እና የኮሙኒኬሽን ድርጅቶች፣ የሲቪክ ማኅበረሰብ ድርጅቶች፣ የመገናኛ ብዙኃን ወይም የስልጠናና ትምህርት ሰጪ ተቋማት፣ እንዲሁም በእነዚህ ተቋማት የሚሠሩ፣ የሚሰለጥኑ፣ የሚማሩ እና የሚያስተምሩ ግለሰቦች እራሳቸውን ወክለው/በግል መሳተፍ ይችላሉ።

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ በሁለተኛው ዙር ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል መክፈቻ ባደረጉት ንግግር “የኪነጥበብ ሥራዎች ወደውስጣችን እንድንመለከት የሚረዱ፣ አንድነት እና ሰብአዊነትን የሚያወሱ፣ እንዲሁም እርስ በእርስ መከባበርንና መዋደድን የሚያስተምሩ፤ በተመሳሳይ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫልን የመሳሰሉ መድረኮች የኪነጥበብ ሰዎችን ለተሻለ ራዕይ በማነሳሳት እና ለአንድ ዓላማ በማስተባበር ያላቸውን ድርሻ የሚታሰብበትም ፌስቲቫል ጭምር ነው” ማለታቸውን አስታውሰው፤ “ በዚህ ውድድር በተለይም ወጣቶች እና ታዳጊዎች እንዲሁም በኪነጥበብ ዘርፍ ባለሞያዎችን ጨምሮ በኪነጥበብ ሥራ ለመሰማራት ያቀዱ እና ሰብአዊ መብቶች ባህል የሆኑባት ኢትዮጵያን ለማየት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ ለማድረግ የሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ጥሪያችንን እና ግብዣችንን ተቀብለው እንዲሳተፉ እንጠይቃለን” ብለዋል።


ስለ ፊልም ፊስቲቫሉ እና ውድድሩ ተጨማሪ ዝርዝር እና የተሟላ ማብራሪያ እዚህ ተያይዟል

የፎቶግራፍ እና የአጫጭር ፊልም ውድድሮች የተሳትፎ ቅጽ እና የውድድሩ አጠቃላይ መመሪያዎች እና ደንቦች


EHRC’s Annual Human Rights Film Festival 3rd edition: Photography and Short Film Competitions Launched on October 3, 2023

Related posts

November 4, 2023November 9, 2023 3rd Film Festival
የኢሰመኮ 3ኛ ዙር የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል የፎቶግራፎች እና የአጫጭር ፊልሞች ውድድር እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ተራዘመ
December 11, 2023December 20, 2023 3rd Film Festival
የኢሰመኮ ሦስተኛው ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በይፋ ተጀመረ
December 6, 2021October 3, 2023 1st Film Festival
ለመጀመሪያ ጊዜ የሚደረግ ዓመታዊ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ፊልም ፌስቲቫል በአዲስ አበባ፣ በአዳማ እና በሀዋሳ ከተሞች ይዘጋጃል
November 30, 2021October 3, 2023 1st Film Festival
ኢሰመኮ እና ኢሰመድህ በኅዳር እና በታኅሣሥ ወራት 2014 ዓ.ም. ታስበው የሚውሉ ዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ቀናትን በተለያዩ ዝግጅቶች ያከብራሉ

Signup for the Latest Update from EHRC

Submit your email to singup
Facebook Like us on FacebookXFollow us on XYouTube Follow us on YouTubeLinkedin Follow us on LinkedinWhatsApp WhatsAppTikTok TikTokTelegram TelegramInstagram InstagramFlicker Flickr

Useful Links

  • NANHRI
  • GANHRI
  • OHCHR
  • ACHPR
  • TRANSITIONAL JUSTICE

Get Involved

  • Jobs
  • Events
  • Contact Us
  • Telegram Bot
  • Subscribe to our newsletter

Connect with Us

  • Facebook
  • Twitter
  • LinkedIn
  • YouTube
  • Flickr
  • Instagram
Descriptive Text

We are an independent
national human rights
institution tasked with
the promotion and protection of human
rights in Ethiopia.

Submit your email to get the latest update from EHRC

Address: Sunshine Tower No. 5, Meskel Square, on Bole Road next to Hyatt Regency Hotel, Addis Ababa, Ethiopia
Tel: +251115504031 | Fax: +251 11 550 4125 | PO Box 1165 Addis Ababa | Email: info@ehrc.org


The contents of this website, excepting third party content for which the Commission bears no responsibility,
may be freely used and copied for educational and other non-commercial purposes, provided that any such reproduction is accompanied by an acknowledgement of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC). Source of images used in the content of this website: EHRC Media and Communications Department Archive and Creative Common License.

This website is managed by the Media and Communications team of the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC).

We are using cookies to give you the best experience on our website.

You can find out more about which cookies we are using or switch them off in .

Scroll to top
  • About
    • Who We Are
    • Our Team
    • Careers
    • Contact Us
  • Regions
    • Addis Ababa
    • Afar
    • Amhara
    • Benishangul Gumuz
    • Central Ethiopia
    • Dire Dawa
    • Gambella
    • Harari
    • Oromia
    • Sidama
    • Somali
    • South Ethiopia
    • South West Ethiopia Peoples’
    • Tigray
  • Areas of Work
    • Economic, Social & Cultural Rights
    • Civil & Political Rights
    • IDPs, Refugees & Migrants’ Rights
    • Rights of Persons with Disabilities & the Rights of Older Persons
    • Human Rights Monitoring & Investigation
    • Women’s & Children’s Rights
    • Human Rights Education
    • Human Rights Film Festival
    • Human Rights Moot Court Competition
  • Press Releases
  • Reports
  • Media
    • EHRC on the News
    • EHRC Newsletters
    • EHRC Videos
    • EHRC Visuals
  • Latest
    • Expert Views
    • Explainers
    • Event Updates
    • Annual Ethiopia Human Rights Situation Reports
  • Resources
Facebook XYouTube Linkedin Flicker TikTok Instagram WhatsApp Telegram
Search
Ethiopian Human Rights Commission - EHRC
Powered by  GDPR Cookie Compliance
Privacy Overview

This website uses cookies so that we can provide you with the best user experience possible. Cookie information is stored in your browser and performs functions such as recognising you when you return to our website and helping our team to understand which sections of the website you find most interesting and useful.

Strictly Necessary Cookies

Strictly Necessary Cookie should be enabled at all times so that we can save your preferences for cookie settings.

If you disable this cookie, we will not be able to save your preferences. This means that every time you visit this website you will need to enable or disable cookies again.