የአፍሪካ ሕፃናት መብቶችና ደኅንነት ቻርተር፣ አንቀጽ 24 (1 እና 6)
የጉዲፈቻ ሥርዓትን የተቀበሉ አባል ሀገራት የሕፃኑ ጥቅም ከሁሉም በላይ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ መሆኑን ማረጋገጥ አለባቸው። እንዲሁም:-
- የጉዲፈቻን ጉዳይ ለመወሰን ሥልጣን የተሰጣቸው አካላትን ማቋቋም እና ጉዲፈቻው ተፈጻሚነት ካላቸው ሕጎች እና ሥነ-ሥርዓቶች ጋር በተጣጣመ መልኩ እንዲሁም አግባብነት ባላቸው አስተማማኝ መረጃዎች መሠረት መከናወኑን እና የሕፃኑ ወላጆች፣ዘመዶች ወይም አሳዳጊዎች አስፈላጊ ሲሆን አግባብነት ያላቸው የሚመለከታቸው ሰዎች ተገቢ ምክር ላይ በመመሥረት ጉዲፈቻውን መቀበላቸውን ማረጋገጥ እና
- የጉዲፈቻ ልጁን ደኅንነት ለመከታተል የሚያስችል አሠራር መዘርጋት አለባቸው።