የዓለም አቀፉ የሥራ ድርጅት ስምምነት ቁጥር 155 – የሥራ ላይ ደኅንነት እና ጤና ስምምነት፣ አንቀጽ 16
- አሠሪዎች በቁጥጥራቸው ሥር ያሉ የሥራ ቦታዎች፣ ማሽኖች፣ መሣሪያዎች እና የአሠራር ሂደቶች ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ደኅንነታቸው የተጠበቀ እና ምንም የጤና ሥጋት የማያስከትሉ መሆናቸውን እንዲያረጋግጡ ሊደረጉ ይገባል፤
- አሠሪዎች ተገቢውን የመከላከያ እርምጃ ሲወስዱ፣ በቁጥጥራቸው ሥር ያሉ ኬሚካላዊ፣ ቁሳዊ እና ሥነ-ሕይወታዊ ንጥረ-ነገሮች እና መሣሪያዎች ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ለጤና አደጋ የሌላቸው መሆኑን እንዲያረጋግጡ ሊደረጉ ይገባል፤
- የአደጋ ሥጋትን ወይም አሉታዊ የጤና ተጽዕኖዎችን ምክንያታዊና ተግባራዊ ሊሆን በሚችለው መጠን ለመከላከል አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝ አሠሪዎች በቂ የደኅንነት መጠበቂያ ልብሶችንና መሣሪያዎችን እንዲያቀርቡ ሊደረጉ ይገባል።