የኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት፣ አንቀጽ 20(5)
- የተከሰሱ ሰዎች በመረጡት የሕግ ጠበቃ የመወከል ወይም ጠበቃ ለማቆም ዐቅም በማጣታቸው ፍትሕ ሊጓደል የሚችልበት ሁኔታ ሲያጋጥም ከመንግሥት ጠበቃ የማግኘት መብት አላቸው።
የሲቪል እና ፖለቲካ መብቶች ዓለም አቀፍ ቃልኪዳን፣ አንቀጽ 14 (3) (መ)
- ማንኛውም ሰው በቀረበበት የወንጀል ክስ በተገኘበት የመዳኘት እና ራሱን በግሉ ወይም በመረጠው ጠበቃ በኩል የመከላከል፣ ጠበቃ ከሌለው ይህ መብት ያለው መሆኑ እንዲገለጽለት መብት አለው።