Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 14
  • File Size 1.34 MB
  • File Count 1
  • Create Date May 13, 2025
  • Last Updated May 13, 2025

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው የተገኙ ሕፃናት ማቆያና ተሐድሶ ተቋም ላይ የተከናወነ የሰብአዊ መብቶች ክትትል ሪፖርት

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ከመጋቢት 4 እስከ መጋቢት 6 ቀን 2016 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በወንጀል ነክ ነገር ውስጥ ገብተው በማቆያና ተሐድሶ ተቋም ውስጥ በሚገኙ ሕፃናት የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ክትትል አከናውኗል። መረጃዎችና ማስረጃዎችን ለማሰባሰብ በተሐድሶ ተቋሙ ከሚኖሩ 16 ሕፃናት፣ 14 የተሐድሶ ተቋሙ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም 5 ጉዳዩ የሚመለከታቸው የመንግሥት ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በአጠቃላይ ከ35 ሰዎች ጋር ቃለ መጠይቆች ተደርገዋል። በተጨማሪም በተሐድሶ ተቋሙ ከሚኖሩ ሕፃናት እና ከተቋሙ ሠራተኞች ጋር 2 የቡድን ውይይቶች እንዲሁም በሕፃናት ማደሪያ ክፍሎች፣ በሕክምና አገልግሎት መስጫ ሥፍራዎች፣ በመማሪያ ክፍሎች፣ በመጸዳጃ እና መታጠቢያ ቤቶች፣ በምግብ ማብሰያ ክፍሎች እና በምድረ ግቢው አጠቃላይ አካባቢያዊ ሁኔታ ላይ ያተኮሩ 6 የመስክ ምልከታዎች ተካሂደዋል። ኢሰመኮ በክትትሉ የደረሰባቸውን ቀዳሚ ግኝቶች ለባለድርሻዎች ለማጋራትና ተግባራዊ ሊደረጉ የሚገባቸው መፍትሔዎች ላይ ምክክር ለማድረግ ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም. የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ የነበረ ሲሆን፤ መጋቢት 9 ቀን 2017 ዓ.ም. የምክረ ሐሳብ አፈጻጸም ክትትል አከናውኗል።

⬇️ የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች እዚህ ተያይዟል