ዛሬ በኢትዮጵያ በሚገኘው የአውሮፓ ኅብረት ልዑክ ቅጥር ግቢ በተካሄደው የሽልማት ሥነ ሥርዓት ከተሻላሚዎቹ አንዱ የሆኑት ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ ሽልማቱ ለመላው የሥራ ባልደረቦቻቸውና ኢሰመኮን ለሚደግፉ በሙሉ አበረታች ዕውቅና የሰጠ መሆኑን ተናግረዋል
Upon becoming one of the recipients of the award at a ceremony held at the Delegation of the European Union to Ethiopia today, EHRC Chief Commissioner said the award is an encouraging acknowledgement to his colleagues and to all who support the EHRC
የሲቪል ሰዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት፣ የንብረት ውድመትና ዘረፋ ተባብሶ ቀጥሏል ተባለ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ባለፉት ስድስት ወራት 161 ሲቪሎች መገደላቸውን ይፋ አደረገ። ለአማራ እና ለኦሮሚያ ክልሎች የግጭት ተሳታፊዎች የተኩስ አቁም ጥሪ አቀረበ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በተለይ በአማራ እና በኦሮሚያ ክልሎች በሲቪል ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች ተበራክተው መቀጠላቸውን አስታወቀ። ኮሚሽኑ መንግሥት በሁለቱ ክልሎች ከሚንቀሳቃሱ ታጣቂ ቡድኖች ጋር በሚያደርገው ውጊያ መካከል እንዲሁም ከውጊያ አውድ ውጪ በሚፈጸሙ ጥቃቶች በዜጎች ላይ ሞት እና ከፍተኛ የመብት ጥሰት እየደረሰ ነው ብሏል
የግል ሥራ እና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲ ሠራተኞችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ለማሻሻል ፈጣን የሕግ ማዕቀፍ ማሻሻያ እርምጃ ያስፈልጋል
Everyone shall have the right to freedom of association with others, including the right to form and join trade unions for the protection of his interests
ማንኛውም ሰው ከሌሎች ጋር በማኅበር የመደራጀት ነጻነት አለው፡፡ ይህም ጥቅሞቹን ለማስጠበቅ የሠራተኛ ማኅበራትን የማቋቋም እና አባል የመሆን መብትን ይጨምራል
በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በሶማሊ፣ በሲዳማ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች እጅግ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን አስታወቀ
በግጭት ዐውድ ውስጥና ውጭ የሚፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችንና ሥጋቶችን በአስቸኳይ ማቆምና የአማራና ኦሮሚያ ክልሎችን ጨምሮ ሁሉንም የትጥቅ ግጭቶች በውይይት በመፍታት ዘላቂ ሰላምና የሰብአዊ መብቶች መከበርን ማረጋገጥ ይገባል