የመንግሥት አስተዳደር ሥልጣን መሠረቱ የሕዝብ ፍቃድ መሆን ይኖርበታል፤ የሕዝቡ ፍቃድ የሚገለጸውም በተወሰኑ ጊዜያት በሚካሄዱ ሐቀኛ ምርጫዎች ነው
The will of the people shall be the basis of the authority of government; this will shall be expressed in periodic and genuine elections
በተለያዩ አካባቢዎች ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ተፈናቃዮች መልሰው ስላልተቋቋሙ በተራዘመ የመፈናቀል አውድ ውስጥ ዓመታትን ለማሳለፍ ተገደዋል
በሴቶች ላይ የሚፈጸም ግርዛትና ተደጋጋሚ ግርዛትን ለማስቆም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ማኅበረሰቡን ለማስተማርና ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ በጋራ መሥራት ይጠበቅባቸዋል
በበጀት አመዳደብ ሂደት ሰብአዊ መብቶች ተኮር መሆን ማለት ሀብትን የሰው ልጆችን ባስቀደመ መልኩ ወይም ሰዎችን ማዕከል በሚያደርግ መንገድ መመደብ ነው
በወንጀል ፍትሕ አስተዳደር ሥርዓት ውስጥ የሚያልፉ ሕፃናት ሰብአዊ መብቶችን ለማስከበር መንግሥት እና ሌሎች ባለድርሻዎች ዘላቂ በሆኑ መፍትሔዎች ላይ በመተባበር መሥራት ይጠበቅባቸዋል
ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወይም በሕጋዊ መንገድ ሀገሪቱ ውስጥ የሚገኝ የውጭ ዜጋ በመረጠው የሀገሪቱ አካባቢ የመዘዋወርና የመኖሪያ ቦታ የመመሥረት፣ እንዲሁም በፈለገው ጊዜ ከሀገር የመውጣት ነጻነት አለው
Any Ethiopian or foreign national lawfully in Ethiopia has, within the national territory, the right to liberty of movement and freedom to choose his residence, as well as the freedom to leave the country at any time he wishes to
የጤና መብት እና በግንባታ ዘርፍ ደኅንነቱ የተጠበቀና ጤናማ የሥራ ሁኔታ መብት በተሻለ ሁኔታ እንዲተገበሩ ባለድርሻ አካላት በጋራ ሊሠሩና የበኩላቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል
እ.ኤ.አ. ከ2019 ጀምሮ በየዓመቱ ጥር 4 የሚታሰበውን የዓለም ብሬል ቀን በማስመልከት ብሬል ለዐይነ ስውራን እና ለከፊል ዐይነ ስውራን አስፈላጊ የመገናኛ ዘዴ በመሆኑ መንግሥታት ለብሬል ትምህርት እና ቁሳቁሶች መስፋፋት ምቹ ሁኔታ እንዲፈጥሩ የቀረበ ጥሪ