ጥቃቱ “በኦነግ ሸኔ፣ በአማራ ኢመደበኛ ታጣቂ ኃይሎችና ግለሰቦች በተከታታይ መፈጸሙን” ኢሰመኮ አስታውቋል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽንና የተባበሩት መንግሥታት ባለፈው ዓመት ባደረጉት ጣምራ ምርመራበትግራይ ክልል ውስጥ በነበረው ጦርነት በሰብዓዊነት ላይ የተፈፀመ እና የጦር ወንጀል ሊባሉ የሚችሉ የወንጀል ዓይነቶች መፈፀማቸውን የሚያመለክቱ ማስረጃዎች መገኘታቸውን አመልክተው ነበር
ከሌሎች የተፈናቃይ መጠለያ ጣቢያዎች በተለየ መልኩ ከሕግ አግባብ ውጪ እና የመንቀሳቀስ መብታቸው ተነፍጎ፣ የሰብአዊ ድጋፍ በበቂ ሁኔታ ሳይቀርብላቸው በጃሬ መጠለያ ጣቢያ ለበርካታ ወራት ተይዘው የቆዩ ናቸው ያለው ኮሚሽኑ ተፈናቃዮቹ የሚገኙበትን ሁኔታ ለመመልከት ተደጋጋሚ ጥረት ቢያደርግም ከመንግሥት አካላት አፋጣኝ ምላሽ አለማግኘቱን ተናግሯል
ኢሰመኮ መንግስት ስላልተባበረው በአዋሽ ሰባት ያሉትን ተፈናቃዮች መጎብኘት እንዳልቻለ ገልጿል
ኢሰመኮ መንግስት ስላልተባበረው በአዋሽ ሰባት ያሉትን ተፈናቃዮች መጎብኘት እንዳልቻለ ገልጿል
በአፋር ክልል መንግሥት በሰመራና አጋቲና የተባሉ ሁለት መጠለያዎች ውስጥ ለደኅንነታቸው በሚል ተይዘው ከቆዩ ዘጠኝ ሺህ አሥር ያህል የትግራይ ተወላጆች የሰመራዎቹ ሙሉ በሙሉ ወደ ቀደመ ቀያቸው አብአላ ከተማ መመለሳቸው የሚያስመሰግን ተግባር መሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ተናገረ
‹‹የማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን ግጭትን በሚቀንስ መንገድ ቢሆን ዓመቱ በጣም ሰላማዊ ይሆናል›› ራኬብ መሰለ፣ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ምክትል ዋና ኮሚሽነር
የኢሰመኮ ሪፖርት እንደሚያስረዳው፣ ለሁለት ቀናት የዘለቀው ጥቃት አገምሳ፣ ጆግ ምግር፣ ታም ኢላሙና ጀቦ ዶባንን ጨምሮ ኡሙሩ ወረዳ በሚገኙ ዘጠኝ ቀበሌዎች ላይ የተፈጸመ ነው፡፡ በእነዚህ ቀበሌዎች በተፈጸሙት ጥቃቶች የተገደሉት ‹‹የኦሮሞ ብሔር ተወላጅ›› ነዋሪዎች መሆናቸውን ኮሚሽኑ አስታውቋል
በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን ኡሙሩ ወረዳ፣ ታጣቂዎች ለሁለት ቀናት በፈጸሟቸው ጥቃቶች ከ60 በላይ ሰዎች ተገድለው ከ70 በላይ ሰዎች መቁሰላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታወቀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ኢሰመኮ ዛሬ አመሻሹን ባወጣው ጋዜጣዊ መግለጫ ባለፈው ሳምንት ከማክሰኞ ጀምሮ እስከ ሃሙስ ቀጥሎ ነበር ባለው ንጹሃን ዜጎች ላይ ባነጣጠረው የሆሮ ጉዱሩ ወለጋ አሙሩ ወረዳ አገምሳ ከተማው የታጣቂዎች ጥቃት፤ ቢያንስ ከ60 በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ሲገደሉ ከ70 በላይ ከከባድ እስከ ቀላል የመቁሰል አደጋን አስተናግደዋል፡፡ እንደ ኮሚሽኑ መግለጫ ከ20 ሺህ በላይ የከተማዋ ነዋሪዎች ደግሞ ወደ ወረዳው ከተማ ኦቦራ ተፈናቅለዋል