ግጭት ባለበት አካባቢ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶች ዓለም አቀፍ ስልቶችን ጭምር በመጠቀም የማጣራት ሥራ እንደሚሠራ ተናግረዋል
ኢሰመኮ ለሴቶችና ሕፃናት መብት ኮሚሽነርነት፤ በዕድሜ ከ35 በላይ ሆና የፖለቲካ ድርጅት አባል ያልሆነች፣ የመብት ተቆርቋሪነትና የሙያ ብቃት አላት ብለው የሚያምኗትን ኢትዮጵያዊት እስከ ሚያዚያ 22 መጠቆም እንደሚቻል ገለፀ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ካሉት አምስት ኮሚሽነሮች መካከል አንዷ በነበሩት የሴቶች እና ህጻናት መብቶች ዘርፍ ኃላፊ ምትክ፤ አዲስ ኮሚሽነር በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ሊሾም ነው። ለተተኪ ኮሚሽነርነት ዕጩ የሚሆኑ ግለሰቦች ጥቆማ ከዛሬ ጀምሮ ለተከታታይ 15 ቀናት እንደሚካሄድም ተገልጿል
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በወንጀል ፍትህ ሥርዓት ውስጥ የጥቃት ተጎጂ ሴቶች እና ህፃናትን መብቶች አያያዝን በተመለከተ ያደረገውን የክትትል ሪፖርት ይፋ አደረገ
በወንጀል ፍትሕ ሥርዓት ውስጥ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶች፣ በወንጀል ሥነ ሥርዓትና በማስረጃ ደንቦች ባለመካተታቸው፣ የጥቃት ተጎጂ ሴቶችና ሕፃናት ፍትሕ እንዳያገኙ ማድረጉን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (አሰመኮ) አስታወቀ
ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች በማቆያ ቤቶች እና በማረሚያ ቤቶች ረዘም ላለ ጊዜ ከመቆየታቸው አንጻር የመተዳደሪያ ገቢያቸውን የሚያጡ መሆናቸው እንዲሁም ለጥሰቶቹ የመፍትሔ እና የካሳ ሥርዓት አለመኖሩ በእነዚሁ ብሔራዊ ምርመራ መድረኮች የተለዩ ተጨማሪ ክፍተቶች ናቸው
የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ “ነጻነታቸውን የተነፈጉ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች የሚጣሱባቸውን ዐውዶች በመመርመር፣ የጥሰት መንስኤዎችን እልባት ለመስጠት፣ ጥሰቶችን ለማስቆም፣ በጥሰቶች ተሳታፊ የሆኑ አጥፊዎችን ተጠያቂነት ለማረጋገጥ እና ለተጎጂዎች ተገቢ የሆነውን የካሳ ሥርዓት ለመዘርጋት እንዲሁም ይህንኑ በሥራ ላይ ለማዋል የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት ቁርጠኛ ሊሆኑ ይገባል” ብለዋል
Perpetrators, as outlined in the report, encompass militias, kebele administrators, police officers, members of special police units, National Defense Forces personnel, prison staff, and government officials
A first-of-its-kind report compiled by the Ethiopian Human Rights Commission (EHRC) implicates federal and regional security forces in widespread constitutional breaches across the country over the last few years
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ለአምስት ዓመታት በአማራ፣ ኦሮሚያ፣ ሶማሌ እና የቀድሞ ደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልሎች ያካሄደውን የዜጎች ነጻነት የተመለከተ ብሔራዊ ምርመራ ይፋ አደረገ