በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች በግጭት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት፤ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም በማድረግ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ ለማፈላለግ በቁርጠኝነት እንዲሠሩ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በድጋሚ ጠይቋል
ኮሚሽኑ በግጭት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም እንዲያደርጉ ጠይቋል
በኢትዮጵያ የግጭት ዐውድ ውስጥ ባሉ አምስት ክልሎች ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ የታጠቁ ሰዎች ባደረሱት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አሳወቀ። ኢሰመኮ የዘፈቀደ፣ የጅምላና የተራዘመ እሥራትና የተፋጠነ ፍትሕ እጦት፣ አስገድዶ መሰወር፣ እገታና የሀገር ውስጥ መፈናቀል እሳሳቢ መሆናቸውን ጠቅሷል
በግጭት ተሳታፊ የሆኑ ሁሉም አካላት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ተኩስ አቁም በማድረግ ለግጭቱ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲያፈላልጉም ኮሚሽኑ በድጋሚ ጠይቋል
በልምድ ልውውጥ መድረኩ ከኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን፣ ከኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ እምባ ጠባቂ ተቋም እና ከኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ የተወጣጡ የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል
ከኢሰመኮ ተጠባባቂ ዋና ኮሚሽነር ራኬብ መሰለ ጋር የተደረገ ቆይታ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋሪያ፣ በጾታ ዕኩልነት ላይ በአማካሪነት የሚሠሩት ወይዘሮ አሻም አሳዝነው፤ የጾታ ዕኩልነት አዶቮኬት የሆኑት ርብቃ ዳዊት እና ረዳት ፕሮፌሰር ሱራፌል ወንድሙ በውይይቱ ተሳትፈዋል
ኢሰመኮ የሰዎች እገታ እየተበራከት ነው አለ
ኢሰመኮ በዚህ መግለጫው የእገታ ጉዳዮች ለማሳያነት አቅርቧል
ታጣቂዎች የሚፈጽሟቸው የእገታ ተግባራት ከዓለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች ጋር የሚቃረን በመሆኑ ከድርጊታቸው መቆጠብ እንደሚኖርባቸው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል