ብሔራዊ ምርመራ ውስብስብና ተደጋጋሚ የሆኑ እና በሀገር አቀፍ ደረጃ ወይም በበርካታ አካባቢዎች የሚታዩ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በጥልቀት ለመመርመር እና ስልታዊና ዘርፈ ብዙ መፍትሔዎችን ለማፈላለግ የሚጠቅም ዘዴ ነው
በግጭቶች የተጎዱ ሰዎችና አካባቢዎችንም መልሶ ለመጠገን እና ለማቋቋም በቂ የሰብአዊ እርዳታ አቅርቦት ያስፈልጋል
የፌዴራል እና የክልል የፀጥታ አካላት በአፋጣኝ የተያዙ ሰዎች የሚገኙበትን ቦታ እንዲገልጹና ተዓማኒ ክስ የማይቀርብ ከሆነ በአፋጣኝ እንዲለቀቁ እንዲያደርጉ ኢሰመኮ በአጽንዖት ያሳስባል
በብሔር ማንነት ላይ የተመሰረተ ሕገ ወጥ እና የዘፈቀደ እስር በመሆኑ በአፋጣኝ ሊለቀቁ ይገባል፤ ወደ መኖሪያ አካባቢያቸውም እስኪመለሱ ድረስ በካምፑ ውስጥ ለመቆየት የሚፈልጉ ሰዎች ቢኖሩ በሙሉ ፈቃደኝነትና ያለ ማናቸውም ዓይነት የእንቅስቃሴ ገደብ ሊሆን ይገባል
የምክረ ሃሳቦች አፈጻጸምን የመከታተልና ሪፖርት የማቅረብ ተቀዳሚ ኃላፊነት የመንግሥት ቢሆንም ሲቪል ማኅበራት ይህንን አስመልክቶ የራሳቸውን ምልከታ ሪፖርት ለማቅረብ ልዩ ዕድል አላቸው