Full recovery and operationalization of basic services sectors such as education and health; full functionality of the law enforcement sector still a significant challenge
በተጎጂዎች ፍላጎት እና ቅድሚያ በሚሰጧቸው ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ትኩረት በማድረግ፣ ያለፉ ጥሰቶችን በሚመጥን መልኩ ምላሽ ለመስጠት፣ ፍትሐዊና ሰላማዊ የወደፊት ነገን ለመመሥረት፣ እንዲሁም ሀገራዊ አንድነትን ለማጎልበት፣ እውነተኛ፣ ሁሉን አቀፍና የተሟላ የሽግግር ፍትሕ ሂደት ተግባራዊ ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን የሪፖርቱ ግኝቶች አጉልተው ያሳያሉ
Findings highlight the necessity of implementing a genuine, inclusive, and comprehensive transitional justice process, with a strong focus on the needs and priorities of victims, to confront past violations, establish a just and peaceful future, and foster national cohesion
በሀገር ውስጥ በሴቶች እና በሕፃናት የመነገድ ድርጊትን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር ሁሉን አቀፍ ሕጋዊ፣ ፖለቲካዊ፣ አስተዳደራዊ እና ማኅበራዊ ስልቶች ሊነደፉ ይገባል
በኢትዮጵያ የስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎች ሰብአዊ መብቶች አጠባበቅ ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ለማረም ትኩረት ሰጥቶ መሥራት ያስፈልጋል
መንግሥት ለተፈናቃዮች ጥበቃ እና ድጋፍ የሚሰጥና የሚያስተባብር በግልጽ ሥልጣን የተሰጠው ተቋም በማቋቋም ወደ ሥራ ማስገባት ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ተግባር ነው
በሕግ፣ በፖሊሲና በአሠራር ረገድ የኮሚሽኑን ምክረ ሐሳቦች ተግባራዊ በማድረግ ለሴቶች እና ለሕፃናት መብቶች የተሻለ ጥበቃ ማድረግ ይገባል
ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ መብቶች ዘርፍ በ2016 ዓ.ም. የተሻለ ትኩረት ሊሰጠው የሚገባ ዘርፍ ሲሆን፤ የፖሊሲና የሕግ ማሻሻያን ጨምሮ ጠንካራ የክትትልና የድጋፍ ሥርዓት መዘርጋት ያስፈልጋል
አካል ጉዳተኞች እና አረጋውያን ከተቋማዊ የአሠራር ክፍተቶችና ከተሳሳቱ አመለካከቶች የተነሳ የሚገጥሟቸውን መሰናክሎች ለመቅረፍ ወጥ ተቋማዊ መዋቅር መዘርጋት ያስፈልጋል
ኮሚሽኑ ክትትል ባደረገባቸው ቦታዎች ከታዩ መለስተኛ የምርጫ አስተዳደር ግድፈቶች ውጭ አጠቃላይ ሕዝበ ውሳኔው ሰላማዊ፣ ሥርዓታዊ እና ከጎላ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ነጻ የነበረ ነው