Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 8
  • File Size 353.64 KB
  • File Count 1
  • Create Date March 26, 2024
  • Last Updated April 8, 2024

አንኳር ጉዳዮች:- ነጻነታቸውን በተነፈጉ ሰዎች ዙሪያ የተደረገ ብሔራዊ ምርመራ

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ/ኮሚሽኑ) ከሚያዝያ 2010 ዓ.ም. እስከ ሚያዝያ 2015 ዓ.ም. ባሉት አምስት ዓመታት ነጻነታቸውን በተነፈጉ ሰዎች መብቶች ዙሪያ በአራት ክልሎች ባከናወናቸው 4 ብሔራዊ ምርመራ /National Inquiry/ የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶችን እና ምክረ ሐሳቦችን ያጠናቀረ ባለ 130 ገጽ ሪፖርት ይፋ አድርጓል።

ብሔራዊ ምርመራ (ግልጽ የአቤቱታ መቀበያ መድረክ) ማለት ውስብስብና ተደጋጋሚ በመሆናቸው፣ አልያም በሀገር አቀፍ ደረጃ ወይም በበርካታ አካባቢዎች የሚታዩ፣ በርካታ ሰዎችን (በተለይም ሕፃናትን፣ ሴቶችን፣ የአካል ጉዳተኞችን) የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ሰለባዎች የሚያደርጉ ጉዳዮች ላይ በጥልቀት ለመወያየትና ዘላቂ መፍትሔዎችን ለማፈላለግ የሚጠቅም ዘዴ ሲሆን፣ እያንዳንዱ መድረክ በአማካይ ለ4 ቀናት የሚቆይ ነው። ኢሰመኮ ይህንን ለሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የምርመራ ስልት ለማስተዋወቅ የካቲት 10 ቀን 2014 ዓ.ም. ከፌዴራልና ከዘጠኝ ክልሎች የተውጣጡ የፖሊስ ኮሚሽነሮች፣ የፍትሕ ተቋማት ተወካዮች እና የተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በአዲስ አበባ ከተማ ስብሰባ ማካሄዱ የሚታወስ ነው። የብሔራዊ ምርመራው ዓላማ የነጻነት መብት ጥሰቶችን መመርመርና መሰነድ፣ ተጎጂዎች የደረሰባቸውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እንዲናገሩ፣ እንዲሁም አቤቱታ የቀረበባቸው ጉዳዩ የሚመለከታቸው ልዩ ልዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ለጉዳዩ ወዲያውኑ ምላሽ እንዲሰጡበት የሚያስችል መድረክ መፍጠር፣ በሁሉም ባለድርሻ አካላት መካከል የውይይት ዕድል ማመቻቸት፣ በዘፈቀደ እስራት መንስኤዎችና ችግሩን በሚያባብሱ እና በሚያወሳስቡ ሁኔታዎች ዙሪያ ግንዛቤ ማሳደግ እና የመፍትሔ ሐሳቦችን ማቅረብ ነው።

ነጻነታቸውን በተነፈጉ ሰዎች ዙሪያ የተደረገ ብሔራዊ ምርመራ

Executive Summary: National Inquiry into Persons Deprived of Liberty