Download
Download is available until [expire_date]
  • Version
  • Download 126
  • File Size 2.64 MB
  • File Count 1
  • Create Date October 28, 2024
  • Last Updated October 30, 2024

የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ዓመታዊ ሪፖርት (ከሰኔ ወር 2015 ዓ.ም. እስከ ሰኔ ወር 2016 ዓ.ም.)

ይህ ሦስተኛው የዘርፍ ሪፖርት ኢሰመኮ ሰኔ 28 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ካደረገው የኢትዮጵያ ዓመታዊ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ሪፖርት በተጨማሪነት የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች የሰብአዊ መብቶች ሁኔታን በተመለከተ የለያቸውን መልካም ጅማሮዎች፣ አሳሳቢ ሁኔታዎችን እና ምክረ ሐሳቦችን አካቷል።

ኢሰመኮ በአማራ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሐረሪ፣ በኦሮሚያ፣ በሶማሊ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በትግራይ ክልሎች በግጭት እና በተፈጥሮ አደጋ መንስኤዎች የተፈናቀሉ ከ333 ሺህ በላይ የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮችን፣ ተመላሾችን እና ወደ ሌላ ቦታ እንዲሰፍሩ የተደረጉ ተፈናቃዮችን የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል እና ምርመራ በማካሄድ ሪፖርቱን አዘጋጅቷል። የሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ምዝገባ እና ሰነድ የማግኘት፣ የጸጥታና ደኅንነት፣ ከቦታ ቦታ የመንቀሳቀስ፣ የሰብአዊ ድጋፍ የማግኘት መብት፣ ለመብት ጥሰት ተጋላጭ ለሆኑ ተፈናቃዮች የሚደረግ የልዩ ድጋፍ ሁኔታ እንዲሁም የዘላቂ መፍትሔዎች አተገባበር ሪፖርቱ ትኩረት ያደረገባቸው ዋና ዋና ጉዳዮች ናቸው።

⬇️ የሪፖርቱ አንኳር ጉዳዮች እዚህ ተያይዟል